ዜና ፦ የባቲ ወረዳ አስተዳደር 28 ኢትዮጵያውያን በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ በፖሊስ መያዛቸዉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2/2015 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል፣ በኦሮሞ ዞን፣ የባቲ ወረዳ አስተዳደር መንግስት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ 28 ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ በአካባቢው ፖሊስ መያዛቸዉን አስታወቀ።

የባቲ ወረዳ አስተዳደር እንዳለዉ ከሆነ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር በተደጋጋሚ እየተከሰተ ይገኛል። በትናንትናው ዕለትም 28 ሰዎች፤ 9 ወንዶች እና 19 ሴቶች፤ በድምሩ 28 ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ለመዉጣት ሲሞክሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ይሁን እንጂ ቢሮው 28ቱ ኢትዮጵያውያን የመጡበትን አካባቢም ሆነ እንዴት በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ለመዉጣት ሲሞክሩ እንደታሰሩ የገለጸው ነገር የለም።

አካባቢው የሰዎች አዘዋዋሪዎች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሰዎች ዝውውር ሰለባዎችን በማምጣት በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት እንደሚጠቀሙበት በጥናት የተረጋገጡ ማስረጃዎች ያመላክታሉ። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.