ዜና፡- ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በመቶ ሺ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ

በብሩክ አለሙ @Birukalemu21

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1/2015 ዓ.ም፡- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በ100ሺ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቅና በውጪ ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ውሳኔ ማስተላለፉን ጠበቃው አቶ አዲሱ አልጋው ለአዲስስታንዳርድ ተናገሩ፡፡

ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ20ሺ ብር ዋስ እንዲለቀቅ በሰጠው ውሳኔ ላይ ዓቃቢ ህግ ይግባኝ በማለቱ ሳይለቀቅ ቆይቷል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህጉንና የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚነቀፍበት ምክንያት ባለማግኘቱ የዋስትና መብቱ ተጠብቆለት በውጪ ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ሲል የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን  አቶ አዲሱ ገልፀዋል፡፡

ጎበዜ ከሀገር እንዳይወጣ እግድ ስላለበት እሱ እንዲከበርም ውሳኔ መሰጠቱን የገለፁት ጠበቃ አዲሱ የዋስትና መጠኑ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ20ሺ ብር ዋስትና እንዲለቀቅ የወሰነውን ውሳኔ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግን ተፈፀመ ከተባለውና ክስ ከተመሰረተበት የወንጀል ክብደት አንፃር በቂ ነው ብሎ ስላላመነበት የዋስትና መጠኑን ወደ 100 ሺ  ከፍ አድርጎታል ብለዋል፡፡

የፌዴራል ዐቃቤ ህግ የሃሰት ወሬን ነዝተዋል ፣ በውጊያ ውስጥ የወገን ጦር አሰላልፍና ቦታን ለጠላት እና ለህዝብ አሳውቀዋል በሚል እና በሌሎች ወንጀሎች ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ ጋዜጠኛ መዐዛ መሃመድ እና ደራሲና አክቲቪስት አሳዬ ደርቤ ላይ መስከረም 20/2015 ዓ.ም. ክስ አንደተመሰረተባቸው  ይታወሳል፡፡

ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ እና ደራሲ አሳዬ ደርቤ ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለቸው ችሎት እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር መፍታታቸው ይታወቃል፡፡ 

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፤ ‘አማራ ፐርስፔክቲቭ’ ተብሎ የተከፈተ የቲዉትር አካዉንት ላይ በቀን 26/12/2014 ቀርቦ ባደረገዉ ንግግር “ጠቅላላ ህዝቡ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የማይደግፍ ይልቁንም ህወሃት ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ የሚፈልግ እና ወጣቱ ከመንግስት ጎን መሰለፍ የማይፈልግ” አድርጎ በማቅረብ ሰራዊቱ በአካባቢዉ ያለ ህዝብ አይደግፈኝም ብሎ እንዲያስብ በማነሳሳት በህዝብና እና በሰራዊት መካከል ያለዉን መልካም ግንኙነት የሚጎዳ እሳቤ እንዲኖር የሰራ፣ የመንግስት የመከላከል አቅም ላይ ህዝቡ ያለዉን አቋም የሚያፈርስ መረጃ እስተላ

ፏል ሲል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መመስረቱ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም ነሃሴ 30/2014 ዓ.ም በፌስቡክ ገፁ “የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ እና ጥምር ጦሩ የት አካባቢ እንዳለ እና የት አካባቢ ሳይዝ እንደቀረ” በፅሁፉ በመግለፅ በዉጊያ እንቅስቃሴ ዉስጥ የወገን ጦር አሰላለፍ እና ቦታ ከፍተኛ ቁምነገር ሆኖ መያዝ የሚገባዉን ለጠላት እና ለህዝቡ በማጋራት ወንጀል በአጠቃላይ ሶስት ተደራራቢ ክሶች እንደተመሰረተበት ተገልጿል፡፡

አማራ ድምጽ የብይነ መረብ ሚዲያ ባለቤትና ምስራች ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ጳጉሜ 2፣ 2014 ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ ተይዞ በድጋሜ መታሰሩ የታሰረ ሲሆን በእለቱ ማለዳ 2 ሰዓት ላይ የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱና ሲቪል በለበሱ የደህንነት ሰዎች መያዙን ታናሽ ወንድሙ አቶ ከድር ሲሳይ ለአዲስስታንዳርድተናግረዋል

የየኛ ቲቪ የበይነ መረብ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እሁድ ከሚያዝያ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለዘጠኝ ቀናት ወደማይታወቅ ቦታ በጸጥታ ሃይሎች ከተወሰደ በኋላ ግንቦት 1 ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ከእስር ተፈትቶ ነበር።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.