አዲስ አበባ መጋቢት 22፣ 2014:- የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መርማሪ ፖሊስ በጋዜጠኛ አሚር አማን እና በካሜራ ማለሙያው ቶማስ እንግዳ ላይ የጠየቀውን ይግባኝ ውድቅ አደረግ። ፖሊስ ማክሰኞ እለት ሁለቱ ባለሙያዎች እያንዳንዳቸው በ60ሺ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ቢወስንም ይግባኝ ጠይቆ ነበር።
መርማሪ ፖሊስ ማክሰኞ እለት የተላለፈውን የዋስትና መብት በመቃወም ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ይግባኝ በመጠየቁ ከእስር ሳይፈቱ ቀርተዋል። ይህን ተከትሎት ትላንት ረፋድ ላይ መርማሪ ፖሊስ እና የተከሳሽ ጠበቆች በችሎት ቀርበው ተከራክረዋል።
ዛሬ በዋለው ችሎት መርማሪ ፖሊስ ፍርድ ቤት የሰጠው ዋስትና ተነስቶ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ይሰጠኝ ያለ ሲሆን የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ ደንበኞቻቸውን በእስር ለማቆየት እንጂ ምንም የተለየ ስራ እንዳልሰራ አስረድተው ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትእዛዛዝ እዲያፀናላቸው ችሎቱን ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱ የሁለቱን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር በነበሩበት ወቅት ፖሊስ የምርመራ ስራውን በአጥጋቢ ሁኔታ ማድረጉ የሚያጠራጥር መሆኑን ገልጾ የእስር ፍርድ ቤት ያስተላለፈውን የዋስትና መብት ተግባራዊ እንዲሆን ትእዛዝ ሰጥቷል። አስ