ዜና: የአሶሴትድ ፕሬስ ጋዜጠኞች ከሶስት ወር እስራት ቆይታ በኋላ በዋስትና እንዲፈቱ ተፈቀደላቸው

ማህሌት ፋሲል

አዲስ አበባ መጋቢት 20/2014: የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሁለቱ የአሶሴትድ ፕሬስ ጋዜጠኞች ጋዜጠኛ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያ ቶማስ እንግዳ እያንዳንዳቸው የ60 ሺ ብር ዋስ አስይዘው ከእስር እንዲወጡ ፈቀደላቸው።

በዛሬው ችሎት ፖሊስ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀን ጠይቋል። የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቹው ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ደንበኞቻቸውን  በእስር ለማስቆየት እና የእስር ጊዚያቸውን ለማራዘም ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ የፖሊስን የተጨማሪ ቀን ይሰጠኝ ጥያቄን ውድቅ እንዲያደርግ እና ደንበኞቻቸውን በዋስ እንዲፈታላቸው ጥያቄ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱም የሁለቱን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ እንዲፈቱ ወስኗል። 

የካቲት 25 በዋለው ችሎት ፍርድ ቤት ፖሊስ የምርመራውን ውጤት እንዲያቀርብ ማዘዙ እና ተጨማሪ ቀናትን መስጠቱ ይታወሳል። ፖሊስም በበኩሉ ከጋዜጠኞቹ የያዘውን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ለምርመራ ተልኳል ማለት የታወቃል። አሚር እና ቶማስ በታህሳስ ወር የኦሮሞ ነፃነት ጦርን (መንግስት ‘ሸኔ’ ብሎ የሚጠራው) በአለም አቀፍ ደረጃ ያስተዋቅቃሉ ብሎ በፌደራል ፓሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.