ዜና: በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ስደተኞች ከነገ ጀምሮ ወደ አገር ቤት ሊመለሱ ነው

አዲስ አበባ መጋቢት 20/2014: በሳውዲ አረቢያ መንግስት ያሉት ኢትዮጵያውያን  ከረቡዕ መጋቢት 21 ጀምሮ  ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ   የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው ከሳዑዲ አረቢያ የተመለሱ የዜጎችን መልሶ ማቋቋምና ማገገም እንዲከታተል የተቋቋመው ኮሚቴ ሰኞ መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ ስብሰባ አድርጓል።  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ” 16 ተቋማትን የያዘው ኮሚቴ ከ7-11 ወራት ውስጥ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ብሏል።” ሲል ገልጿል።

አዲስ ስታንዳርድ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ለወራት በሳውዲ አረቢያ እስር ቤቶች  ኢሰብአዊ በሆነ ችግር ውስጥ እንዳሉ  ዘግቧል። በርካታ ዘገባዎች የኢትዮጵያውያን እስረኞችን ሁኔታ እንዳረጋገጡት የሳዑዲ ማረሚያ ቤቶች በስደተኞች ላይ የሚወስደው እርምጃ በብዙ ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ነው።

ማረሚያ ቤት ውስጥ በሚገኙ ታራሚዎች በተደረጉ በርካታ ስልክ ጥሪዎች በሰጡት ምስክርነት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው በደል አራስ እናቶች፣ ጨቅላ ሕፃናት እና ነፍሰ ጡር እናቶች ያለ በቂ ምግብ፣ መድሃኒት እና በቂ የመኝታ ሳያገኙ ታስረው እንደሚገኙ አረጋግጠውልናል።

የኢትዮጵያ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በተደጋጋሚ ተማጽኖ የነበረ ሲሆን እስረኞቹ የኤምባሲው ባለስልጣናትን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት አቤቱታቸውን ችላ በማለታቸውና ጥያቄያቻቸው ባለመመለሱ ወቀሳ አቅርበዋል ።ሚኒስቴሩ በዚህ አመት ጥር ወር ላይ መንግስት በወቅቱ መፍትሄ ሊሰጥባቸው በሚገቡ ሌሎች ‘ዋና ዋና ጉዳዮች’ ምክንያት ወደ አገራቸው የመመለስ ሂደቱ ተቋርጦ እንደቆየ ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ “ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ የሚያመቻች የልዑካን ቡድን ተቋቁሞ በቅርቡ ወደ ሳውዲ አረቢያ ያመራል” በማለት በወቅቱ ተናገረው እንደነበር ይታወሳል።

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.