ዜና:- የአረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብረሃ ደስታ ከእስር ተፈቱ

ፎቶ:ማህበራዊ ድህረገፅ

በአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጠኞች

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣2014-ሁለት ወር ከሀያ ሁለት ቀናት እስር ላይ የቆዩት የአረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበርና የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር (የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ) የነበሩት አቶ አብረሃ ደስታ  በፍርድ ቤት ትእዛዝ በ 10,000 ሺብር ዋስትና ከእስር ተፈቱ፡፡

ሰኔ ወር ላይ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ተከራይተው ይኖርቡት ከነበረ ሆቴል መስከረም 20/2014  በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ አብርሀ አራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በተጠረጠሩበት ሁለት  ጉዳዩች ላይ  ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር ሲከራከሩ ቆይተው በ10ሺ ብር ዋስትና ከእስር ወተዋል፡፡

መስከረም 20/2014 በፀጥታ ሀይሎች እንደታሰረ ለአዲስ ስታንዳርድ የተናገሩት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አቶ አብርሀ ደስታ የቅርብ ቤተሰብ “የአራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሀሙስ ታህሳስ 7 2014 በ10ሺ ብር ዋስትና እንዲወጣ ፈቅዶለታል ብለዋል” በዋስትናው መሰረት ሰኞ ከሰአት በኋላ 9 ሰአት ላይ ከእስር ተፈቷል ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.