ዜና: አገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት በሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ

አዲስ አበባ ሰኔ 30፣ 2014 – የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የተደረገውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ መሰረት በማድረግ÷ የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት የታሪፍ ጭማሪ ዛሬ አስታውቋል፡፡ አዲሱ የታሪፍ ጭማሪም ከዛሬ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የጀመረ መሆኑን ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

በዚህም መሠረት የሚከተለው ዝርዝር በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተደረገውን የታሪፍ ጭማሪ ያሳያል፣

 • በደረጃ አንድ በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5360 ሲሆን አዲሱ ታሪፍ 0.5600 ብር በኪሎሜትር ሆኗል፡፡ ጭማሪ በኪሎ ሜትር 0.0240 ሳንቲም ነው፡፡
  ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎሜትር ነባር ታሪፍ 0.6150 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.6464 ነው፡፡ ጭማሪ በሰው በኪሎሜትር 0.0314 ሳንቲም ይሆናል፡፡
 • ደረጃ ሁለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5120 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.5420 ነው፡፡ ጭማሪ 0.0300 ሳንቲም፡፡
  ደረጃ ሁለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5680 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.6054 ብር ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.0374 ሳንቲም፡፡
 • ደረጃ ሶስት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.4750 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.5081 ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.0331 ሳንቲም ነው፡፡
  ደረጃ ሶስት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5360 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.5735 ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.375 ሳንቲም ነው፡፡
  የታሪፍ ስሌቱ በ100 ኪሎ ሜትር ሲታይ
 • በደረጃ አንድ ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 53.60 ሲሆን በአዲሱ ታሪፍ ብር 56.00 ሆኗል፡፡ ጭማሪ በ100 ሊሎሜትር ብር 2:40 ነው፡፡
 • በደረጃ ሁለት ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 51.20 የሚያስከፍል ሲሆን በአዲሱ ታሪፍ ብር 54.20 ሆኗል፡፡ ጭማሪ በ100 ኪሎሜትር ብር 3.00 ነው፡፡
 • በደረጃ ሶስት ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 47.50 የሚያስከፍል ሲሆን በአዲሱ ታሪፍ ብር 50.81 ያስከፍላል፡፡ ጭማሪ በ100 ኪሎ ሜትር ብር 3.31 ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሰራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር በተከናወኑት የዝግጅት ስራዎች ላይ በመመስረት ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ከትናንት ሰኔ 29 ቀን ጀምሮ በሊትር ቤንዚን 47 ብር ከ83 ሳንቲም ፣ ነጭ ናፍጣ 49 ብር ከ02 ሳንቲም ፣ ኬሮሲን ከ49 ብር ከ02 ሳንቲም ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 53 ብር ከ10 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 52 ብር ከ 37 ሳንቲም፣ የአውሮፕላን ነዳጅ 98 ብር ከ83 ሳንቲም እንደሚሸጥ ማስታወቁ ይታወሳል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.