ዜና ትንታኔ፦በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉና የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ መሆን መጀመሩ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ ለሕዝብ ማመላለሻ ረጅም ወረፋ ማየት የተለመደ ሆኗል። ፎቶ ክሬዲት፡ Bjørn Tørrissen የጉዞ ብሎግ

በብሩክ አለሙ

ሰኔ 29፣ 2014 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፦ ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሬ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሰራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲከናወን መቆየቱን ያስታወሰው ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ከዛሬ ሰኔ 29 ቀን ጀምሮ በሊትር ቤንዚን 47 ብር  ከ83 ሳንቲም ፣ ነጭ ናፍጣ 49 ብር ከ02 ሳንቲም ፣  ኬሮሲን ከ49 ብር ከ02 ሳንቲም ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 53 ብር ከ10 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 52 ብር ከ 37 ሳንቲም፣ የአውሮፕላን ነዳጅ 98 ብር ከ83 ሳንቲም እንደሚሸጥ  አስታውቋል፡፡

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር እና የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ትናንት በጋራ በሰጡት መግለጫ የድጎማ ስርዓቱ በአምስት ዓመት ውስጥ ሁሉንም ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ውጭ የሚያደርግ መሆኑም ገልጸዋል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ  መንግስት ለነዳጅ ምርት በዓለም ላይ ካለው ዋጋ በግማሽ በመቀነስ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውሰው አሁን ላይ ጥናትን መሰረት ያደረገ የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ አድርጓል ብለዋል። አክለውም ከዚህ ቀደም በፖሊሲ ያልታገዘ ድጎማ ሲደረግ መቆየቱን ያነሱት ሚኒስትሩ አሁን የነዳጅ ድጎማ ስርዓት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በድጎማ ስርዓቱ ውስጥ ያልተካተቱ ተሽከርካሪዎች በየሶስት ወሩ በሚደረግ ማሻሻያ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከድጎማ ስርዓቱ እንደሚወጡ ጠቁመው ድጎማ የሚደረግላቸው ተሽከርካሪዎችም በአምስት ዓመት ውስጥ ከድጎማ ውጭ ይደረጋሉ ብለዋል።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የነዳጅ ፍጆታ ተቀራራቢ የሊትር መጠን ግምት በጥናት መለየቱና እያንዳንዱ ተሸከርካሪ የሚጠቀመውን የነዳጅ መጠን ያገናዘበ ስሌት በመቀመጡ ተሽከርካሪዎቹ ያለ ብክነት የታለመ የነዳጅ ድጎማን ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያግዝ ነው፡፡

የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎች ብቻ  ዕለታዊ የነዳጅ መጠን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በዚህም መሰረት  በቀን ውስጥ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ሰባት ሊትር፣ ሚኒባስ 65 ሊትር፣ሚዲባስ 94 ሊትር፣ ታክሲ 25 ሊትር፣ የከተማ አውቶብሶች 102 ሊትር፣ የመግስት ሰራተኞች ባስ 25 ሊትር አንዲሁም ሀገር አቋራጭ ተሸከርካሪዎች 65 ሊትር ማግኘት የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

መንግስት በነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሪ ባደረገበት ማግስት ነጋዴውና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በህበተሰቡ ላይ የራሳቸውን ጭማሬ ሲያደረጉ መቆየታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው የተለያዩ የመዲናይቱ የማህበረሰብ ክፍሎች ተናግረዋል

የብሔራዊ የታለመለከት የነዳጅ ድጎማን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል መተግበሪያ በልፅጎ አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ጀምሯልም ነው የተባለው፡፡ በዚህም መሠረት በቴሌ ብር በኩል አገልግሎቱን ለማግኘት የተመዘገቡ ከ160 ሺ በላይ ተሸከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መተግበሪያውን በመጠቀም ይስተናገዳሉ ተብሏል፡፡ 

በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ተፅዕኖ አለው?

ሚያዚያ ወር በተጨመረው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ተፅዕኖ እያሳደረብን ነው ሲሉ የትራንሰፖርት ተጠቃሚዎችና የታክሲ አሽከርካሪዎች መግለፃቸውን አዲስ ስታንዳር መዘገቧ ይታወቃል።

መንግስት የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያውን ተከትሎ በእቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ በመግለፅ ቢያስጠነቅቅም ለአዲስ ስታንደርድ ሃሳባቸውን ያካፈሉ የከተማዋ ነዋሪዎች  ግን  የዋጋው ጭማሬ መኖሩንና የኑሮ ውድነቱ ጭራሹኑ ማየሉን ገልፀዋል፡፡ አክለውም በትራንፖርት ላይም ለከፋ እንግልት መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

መንግስት በነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሪ ባደረገበት ማግስት ነጋዴውና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በህበተሰቡ ላይ የራሳቸውን ጭማሬ ሲያደረጉ መቆየታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው የተለያዩ የመዲናይቱ የማህበረሰብ ክፍሎች ተናግረዋል፡፡ ይህም ድርጊት ቀድሞውኑ ለህዝቡ ከባድ የነበረውን የኑሮ ውድነት ይባስ እንዲያሻቅብ ማድረጉንም አክለው ገልፀዋል፡፡

አዲስ ስታንዳርድ አዲስ አበባ ከተማ መገናኛ አከባቢ ተገኝታ  የታክሲ ሹፌሮችን ያነጋገረች ሲሆን መንግስት በነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሬ ማድረጉን እንጂ ባለ ታክሲዎች ላይ የሚመጣውን ተፅዕኖ ከግንዛቤ ውስጥ አላስገባም ሲሉ ይናገራሉ፡፡ “የነዳጅ ጭማሬውን ምክንያት በማድረግ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ ተደርጎብናል፡፡ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል” ሲሉ በምሬት አክለው ገጸውልናል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ቁምነገር እሸቱ ለአዲስ ስታንዳርድ በተደረገው ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የተነሳ የዋጋ ላይ ግሽበት እንዳይከሰት ከሶስት ወር በፊት የሚቆጣጠር ግብረ-ሀይል ተቋቁሞ ቁጥጥር ለማድረግ ወደ ስራ እንዲገባ መደረጉን ገልፀዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.