ዜና፡ ፌስቡክ በኢትዮጵያ ከሚገኙ አጋሮቹ በጥላቻ ንግግሮች ዙሪያ የሚሰጠውን ምክረ ሀሳብ ወደ ጎን ማለት እንደሚያዘወትር ተጠቆ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2/2015 ዓ.ም፡- ቢዝነስ ኢንሳይደር የተባለ ድረገጽ ያደረገው ምርመራ እንደሚያመለክተው ፌስቡክ የጥላቻ ንግግር በተመለከተ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ከአጋር ድርጅቶቹ የሚሰጠውን ምክረ ሀሳብ ባለመቀበሉ እና ወደ ጎን በማለቱ በሀገሪቱ የተከሰቱ ብጥብጦች እንዲባባሱ አስተዋጽኦ ማድረጉን አመላክቷል።

በአለማችን ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ የማህበራዊ ትስስር ዘዴዎች መካከል ዋነኛው እና ትልቁ የሆነው ፌስቡክ አፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካን እና መካከለኛው ምስራቅ ያለውን ገቢ ሲገልጽ የተቀረው አለም በሚል ይጠራቸዋል። ከነዚህ ሀገራት የሚያገኘው የገቢ መጠንም አስር በመቶውን ብቻ መሆኑንም ኩባንያው ካቀረበው መረጃ መረዳት ይቻላል።

ፌስቡክ በየሀገራቱ የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሀገራቱ ያሉት ተጠቃሚዎቹ ስለሚያጋሩት መልዕክት ይዘት የምክረ ሀሳብ እንዲሰጡት የሚያደርግ ፕሮግራም አለው። ታማኝ አጋሮች በሚል የሚጠራቸው እነዚህ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፌስቡክ ደንበኞቹ በሚያጋሩት መልዕክት ይዘት በተመለከተ የሚቆጣጠርበትን የፖሊሲ እና ትግበራ ምክረ ሀሳብ ያቀርቡለታል።

በኢትዮጵያ የሚገኙ የፌስቡክ አጋር የሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለቢዝነስ ኢንሳይደር የምርመራ ጋዜጠኛ ተኬንድራ ፓርመር እንደገለጹት ከሆነ በኢትዮጵያ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የሚያጋሯቸው መልዕክቶች በተለይም የጥላቻ ንግግር ጋር በተያያዘ የሚያቀርቡት ምክረ ሀሳብ ተቀባይነት አያገኝም። ፌስቡክ ምክረ ሀሳቡቹን ወደ ጎን ስለሚላቸው ብጥብጦችን በማባባስ ከፍተኛ ሚና መጫወቱንም ድርጅቶቹ ገልጸዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.