አዲስ አበባ፣ የካቲት 15/2015 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በግንደወይን ከተማ አስተዳደር የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ወጣት ላይ የአንድ ዓመት ከስምንት ወር የእስራት ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ገለፀ።
ተከሳሽ ዲያቆን ጌታቸው አለልኝ የተባለ ግለሰብ አግባብ ባለው የቤተሰብ ህግ ከተፈቀደው ውጭ ለአካለ መጠን ያልደረሰች ልጅ ለማግባት በማሰብ ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 11፡0ዐ ሲሆን በግ / ወይን ከተማ አስተዳደር ዐ1ቀበሌ ልዩ ቦታው አርሴማ ቤተክርስቲያን ውስጥ የግል ተበዳይ የ 12 ዓመት ህፃንን በተክሊል ወይም በሀማኖት ስርዓት ጋብቻ ፈፅሟል፡፡
በመሆኑም ተከሳሽ በፈፀመው ለአካለ መጠን ያልደረሰችን ልጅ ማግባት ወንጀል ዓ/ህግ የሰውና ጋብቻው ሲፈፀም የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃ በማያያዝ ክስ መስርቶ ተከሳሽም የዓ/ህግ ክስ በችሎት ተሰጥቶት የዓ /ህግ ክስ በችሎት ተነቦለት ክሱን እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ ወንጀሉን መፈፀሙን አምኖ ነገር ግን ህፃናትን ማግባት በቤተክርስቲያ ህግ የተፈቀደ ነው ወንጀል አይደለም በማለት ተከራክሯል፡፡
ፍ/ቤቱም የህግ ምስክሮችን ሰምቶ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ ቁ113/2 / መሠረት ፍ/ቤቱ ወደ ወንጀል ህግ አንቀጽ 648 /ሀ/በመቀየር እንዲከላከል ቢጠይቀውም ተከሳሽ ግን የመከላከያ ምስክር የለኝም በማለት በማመልከቱ በቀን 13/6/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን እና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ያስተምራል ተብሎ የታሰበውን የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ቅጣት ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡አስ
ምንጭ- ጎንቻ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት