ዜና፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ላይ እንቅልፍ ወስዷቸዋል የተባሉትን አብራሪዎቹን ከስራ አግዶ ምርመራ መጀመሩን ገለፀ


ዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13/2014 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች በአየር ላይ እንቅልፍ ጥሏቸው ከአዲስ አበባ አየር ትራፊክ ቁጥጥር ጋር ያለው ግንኙነት ተቋርጦ አውሮፕላኑ መዳረሻውን አንዲያልፍ አድርገዋል የሚል መረጃ እንደደረሰው ገልጾ የበረራውን ሰራተኞች ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ ከስራ በማገዱን አስታወቀ፡፡

ባሳለፍነው ሰኞ ነሐሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው የመንገደኞች አውሮፕላን በረራ ቁጥር ET343 ከካርቱም አዲስ አበባ ሲጓዝ አዲስ አበባ ካለው የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር ያለው ግንኙነት ተቋረጦ ከመድረሻ ሰዓታቸው 25 ደቂቃ ዘግይተው ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ መድረሳቸውን አቪዬሽን ሄራልድ ገልጧል፡፡

የአውሮፕላኑ አውቶ ፓይለት ሲስተም ሥራውን ሲያቋርጥ ባሰማው የማንቂያ ድምጽ ምክኒያት አብራሪዎቹ መንቃታቸው ተገለፀ ሲሆን ከችግሩ ጋር ተያይዞም በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ የበረራ ሰራተኞች ለጊዜው ከስራ ታግደው ምርመራ እየተደረገ ነው ተብሏል።

አየር መንገዱ በሚገኘው የምርመራ ውጤት መሰረት ተገቢውን እርምጃ እንደሚውስድም ጠቅሶ የደንበኞችን ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ የዘወትር ቅድሚያ ተግባሩ መሆኑንና ይህን ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አክሎ ገልጧል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.