ዜና፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት ጥያቄው ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ፈቀደ

ምስል- የፌዴሬሽን ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12/2014 ዓ.ም፡- በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የ6 ዞኖችና የ5 ልዩ ወረዳ በአንድ ክልል የእንደራጅ አቤቱታን ተቀብሎ ከመረመረ በኃላ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የደቡብ ኦሞ፣ የጌዴኦ፣ የኮንሶ ዞኖች፣ እንዲሁም የደራሼ፣ የአማሮ፣ የቡርጂ፣ የአሌ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በጋራ ”የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” የመመስረት ጥያቄ ከሕገ መንግሥቱ አንፃር ውሳኔ ለመስጠት እንዲያስችል የሕዝብን ይሁንታ ማረጋገጥ ስለሚያስፈልግ ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ በሆነ መልኩ ገለልተኛ በሆነው ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አማካኝነት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅና የሕዝብ ውሳኔው ውጤት ሪፖርት ለምክር ቤት እንዲቀርብ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ ዞኖችና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አንድ ላይ የሚቀጥሉ ይሆናል ተብሏል።

የሕዝብ ውሳኔው ሂደት ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና የሕዝብን ሰፊ ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.