አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3/ 2014 ዓ.ም፦የኔዘርላንድ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ ኢትዮጵያን ሲገዛ በነበረው “አረመኔው” ማርክሲስት አገዛዝ በጦር ወንጀለኞች እ.ኤ.አ በ2017 ጥፋተኛ ተብሎ በተጠረጠረው የ67 አመቱ ኢትዮጵያዊ ሆላንዳዊ ላይ የተላለፈበትን የቅጣትና የእድሜ ልክ እስራት ማጽደቁን አሶሴትድ ፕረስ የዜና አውታር ዘገበ።
እንደዘገባው በጦር ወንጀለኞች በሄግ ኔዘርላንድ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የ67 አመቱን ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሆላንዳዊ ዜጋ እ.ኤ.አ 1970ዎች ኢትዮጵያን ሲገዛ በነበረው የደርግ አገዛዝ ተጠርጣሪው ተሳትፈዋል ባለው በጦር ወንጀል የጥፋተኝነት እና የእድሜ ልክ እስራት አጽድቋል።
ታመው ስለነበር ጉዳያቸውን ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቀርበው ለመከታተል ያልቻሉት አቶ እሸቱ አለሙ እ.ኤ.አ በ2017 የተከሰሱበትን የቅጣት ውሳኔዎች ውድቅ ለማድረግ ቢሞክሩም የሄግ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የአለም አቀፍ ወንጀሎች ክፍል በበኩሉ በቀድሞ በመንግስቱ ሀይለማሪም ሲመራ በነበረው በአምባገነኑ የደርግ መንግስት ወቅት ቀይ ሽብር ተብሎ በሚጠራው እ.ኤ.አ በ1977-78 ተቃዋሚን የማጥራት ወንጀል ጥፋተኛ ነህ ብሎ በይኖባቸዋል።
አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት አገዛዙ ተቃዋሚዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋ ሲሆን 150,000 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ምሁራን እና ፖለቲከኞች ተገድሏል ሲል ዘገባው አክሎ አትቷል። የሰብአዊ መብት ጥበቃ (Human Rights Watch) በኢትዮጵያ የተከሰተውን ነገር “በአፍሪካ ውስጥ እስካሁን ከታዩት የጅምላ ግድያ ዘዴዎች አንዱ ነው” ሲል ገልጿል።
እ.ኤ.አ በ1978 የደርግ ጦር በወቅቱ ከነበሩ ተቃዋሚዎች አንዱ ከሆነው ከኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ጋር ሲፋለም አቶ አለሙ በጎጃም ጠቅላይ ግዛት የደርግ ተወካይ ሆነው እንዳገለገሉ ዘገባው አስታውሷል። ፍርድ ቤቱ በግዛቱ ውስጥ የጦር ወንጀሎች የተፈፀሙት “በተከሳሹ እውቀት እና ተሳትፎ” ነው ብሏል።
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማጠቃለያ እንደገለጸው፣ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ተጎጂዎች መካከል ብዙዎቹ ወጣት ተማሪዎች ያለምክንያት ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ታስረዋል እንደነበር ዘገባው አክሎ ገልጿል። የፍርድ ቤቱ ብይንም ከፊሎቹ ከፍተኛ ስቃይ እንደደረሰባቸው አብዛኞቹ ደግሞ ያለፍርድ የእስር እና የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው እንደነበር ይገልፃል።
ፍርድ ቤቱ “የሞት ቅጣቱ የተፈፀመው በተከሳሹ መመሪያ መሠረት አሰቃቂ በሆነ መንገድ ነው” ብሏል።
እ.ኤ.አ. በ2017 ጥፋተኛ ተብለው የተፈረደባቸውን የመጀመርያው ችሎት ላይ ባደረጉት ስሜታዊ ንግግር፣ አቶ አለሙ በደርግ ስለተፈፀሙ ወንጀሎች ክሱን ቢቀበሉትም በግላቸው እንዳልፈፀሙት ለዳኞች ተናግረዋል።
አለሙ በኔዘርላንድ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱን ሲከታተሉ የነበረው እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ወደ ኔዘርላንድ ሄደው በ1998 የኔዘርላንድ ዜግነት ስለተሰጣቸው ነበር።
መንግስቱ ሀይለማሪያም አሁን በስደት በዚምባብዌ እየኖሩ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2006 የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በሌሉበት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው የሞት ፍርድ እንደተፈረደባቸው የሚታወስ ሲሆን ባያዝነው አመት የዚምቧቤ መንግስት ከተጠየቀ ለማስረከብ ፍቃደኛ እንደሆነ መናገሩ ይታወሳል። አስ