አዲስ አበባ፡ ሰኔ 8/ 2014 ዓ.ም.፡- በባህርዳር ከተማ የዘረፋና የስርቆት ወንጀል እየተበራከተ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ላይ ተፅዕኖ እያደረሰ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለኢቢሲ ገለፁ፡፡ ኢቢሲ ያናገራቸው ተበዳዮች እንደገለፁጽ በታክሲ እና ባጃጃ ትርንስርት ላይ ስርቆቱ እያየለ ሲሆን ”በተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀል እየደረሰብን ነው” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
ሚዲያው የነጋገረው እንዱ ተበዳይ በታከሲ ላይ ሁለት ጊዜ የስልክ ስርቆት ተፈፅሞብኛል ሲል አስረድቷል፡፡ ሌላኛው ከተማው ነዋሪ ፓፒረስ የሚባል አካባቢ ኪሱ ዉስጥ ገብተው ስልኩን ለመስረቅ ሲሞክሩ ለማስጣል ሲታገል ነዋሪዉ እያየ ዝም እንዳለ ገልፀል፡፡ ተበዳዩ አክሎም እንደገለፀው ሁለተኛ የስርቆት የተፈፀመነት በጃጃ ላይ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ሌቦቹን ብንይዛቸው ነገ የህግ አካላት ሲለሚለቋቸው ጠላት አናፈራም በማለት ህዝቡ ወንጀል ሲፈፀም እያየ ዝምታን መምረጡን ተበዳዩ ገልጿል፡፡
ይህ በከተማው እየተበራከተ የመጠጣው የወንጀል ድርጊቶች ተሸከርካሪም በመጠቀም እንደሚፈፀምም ነው ነዋሪዎቹ የገለፁት፡፡ ድርጊቱንም የከተማው የፀጥታ አካል ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ምክትል መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌትነት አናገው በበኩላቸው ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በተሰራው ስራ የከተማው ፀጥታ እየተሻሻለ መምጣቱን ለሚዲያው ገልፀዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም የፀጥጣ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተው አየሰሩ በመሆኑ የዝርፊና ስርቆት ወንጀሎችን መከላከል ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው “ባሁን ወቅት የዘረፋና የስርቆት ወንጀል ቀንሷል በፀጥታ አካላት እየተደረገ ባለው ክትትል ህጋዊ እርምጃ እየወሰድን በመሆኑ መረጃውን እያጠናከርን ለፍርድ እያቀረብን ሲለሆነ አሁን ላይ በከተማው ላይ አንፃርዊ ሰላም ተፈጥሯል” ብለዋል፡፡አስ