አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26/2015 ዓ.ም፡- መንግስት የሀገሪቱን የፋይናንስ ስርአት ለውጭ ተፎካካሪ ባንኮች ክፍት ለማድረግ የያዘውን እቅድ ለማሳካት በማለም በቀጣይ አምስት አመታት ውስጥ ለአምስት የውጭ ባንኮች ፈቃድ ለመስጠት ማቀዱን አስታወቀ።
የማዕከላዊ ባንክ ምክትል ገዢ የሆኑት ሰለሞን ደስታ በቀጣይ አምስት አመታት ከሶስት እስከ አምስት ለሚደርሱ ባንኮች ፍቃድ እንሰጣለን ሲሉ ለጋዜጠኞች መናገራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል በዘገባው አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የባንክ አገለግሎት ዘርፍ ትልቁን ድርሻ የሚጫወተው ንግድ ባንክ መሆኑን ያመላከተው ዘገባው በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የተመሰረቱ 29 የግል ባንኮች መኖራቸውንም ጠቁሟል።
የውጭ ባለሃብቶች በተለያዩ አማራጮች የፋይናንስ ዘርፉን መቀላቀል እንደሚችሉ ምክትል ገዢው ጠቁመዋል ያለው የዜና ወኪሉ የሀገር ውስጥ ባንኮች ጋር በሽርክና መስራትን ጨምሮ የራሳቸው የፋይናንስ ተቋም በመመስረት እንዲሰሩ ይፈቀዳል ማለታቸውን አስታውቋል። አስ