በማህሌት ፋሲል
አዲስ አበባ ጥር 18 /2014 የአሐዱ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ አርታኢ የሆነው ክብሮም ወርቁ ዛሬ በቀበሌ መታወቂያ ዋስ ከእስር መፈታቱን ጠበዋቀው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ:: ጠበቃው አቶ ጥጋቡ ለአዲሰ ስታንዳርድ እንደተናገሩት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጥር 5/2014 በዋለው ችሎት “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታው በድጋሚ በአራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እንዲታይ ትእዛዝ ሰቶ ነበር::
ህዳር 3/2014 ዓ.ም የፌደራል የመጀመሪ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ጋዜጠኛ ክብሮምን በ 15000 ብር ዋስትና እንዲወጣ የፈቀደ ቢሆንም አዲስ አበባ ፖሊስ ለአራደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለት ክርክር ያደረገ ሲሆን ህዳር 7/2014 ዓ.ም ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛው በ15000 ብር ዋስትና ይውጣ ሲል ውሳኔ መስጠቱ የሚታወስ ነው :: ጠበቃው አክለውም አካልን ነፃ የማውጣት መዝገባችንን እንደገና ጥር 9/2014 እንከፍታለን ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረው ነበር ::
ጋዜኛ ክብሮም ጥቅምት 16 2014 ዓም በአዲስ አበባ ፖለስ የታሰረ ሲሆን በሚሰራበት ሚዲያ የህወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል የምትገኘውን የሐይቅ ከተማ መቆጣጠራቸውን በሚገልፅ ዜና መሆኑ ይታወቃል:: አስ