ትንተና ፣ በሳውዲ አረቢያ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንዲደርስላቸው ተማጸኑ

እቴነሽ አበራ

አዲስ አበባ ፣ጥር 14/2014 ፣ በያዝነው ጥር ወር እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መንግስት ያደረገላቸውን ‘ታላቁ የኢትዮጵያውያን ወደ ሀገርቤት ጉዞ’ ጥሪ በመቀበል ከአሜሪካ ፣ ከአውሮፓ እና ከሌሎች ክፍላተ አለማት ወደ ኢትዩጵያ ገብተዋል። የገቡት ዜጎች መንግስት ባዘጋጀላቸው እንዲሁም  በተለያዬ ዝግጅቶች ላይ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ሽፋን ሲያገኝ ቆይቷል። በዚሁ ወር አዲስ እስታንዳርድ ሳውዲ አረቢያ ከሚገኙ እስረኞች እና ቤተሰቦቻቸው አስከፊ እና ከሰብአዊነት ያፈነገጠ አያያዛቸውን አስመልክቶ የስልክ መልክቶች ሲደርሱ ቆይተዋል። 

አዲስ እስታንዳርድ በስልክ ያናገራቸው እስረኞች እንደገለፁት የሚያጠቡ እናቶች እና ልጆቻቸው  ነፍሰጡር ሴቶች እንዲሁም ህመምተኞች በአንድ ክፍል ውስጥ ያለ በቂ ምግብ ፣ ህክምና ፣ አልባሳት እና የመተኛ ቦታ ታጉረው ስለሚገኙ የኢትዮጵያ መንግስት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። እስረኞቹ  በእስር ቤት ውሰጥ  ያለውን ከሰብአዊነት ያፈነገጠ አያያዝ፣ በሳውዲ አረቢያ ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ  ሰራተኞች እና ውጭ  ጉዳይ ሚኒስቴርን ቸልተኝነት  ኮንነዋል።

በአማራ ክልል ውስጥ ከሚገኘው የኦሮሞ ልዩ ዞን  የተሰደደችው እና የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ሀያት እንደነገረችን በአንድ ክፍል ውስጥ ከ150 በላይ እሰረኞች ታጉረው ይገኛሉ ። ” በቂ የሆነ ምግብ እያቀረቡልን አይደለም፤ ጠዋት እና ማታ ቁራጭ ዳቦ  ነው የሚሰጡን በዛ ላይ ምንም አይነት ህክምና እያገኘን አይደለም” ትላለች።

ከህክምና ስትመለስ በፖሊሶች የተያዘችው ሀያት ጅዳ ስለ እስር ቤቱ ኑሮ አስከፊነት ስታስረዳ፣ ” የአእምሮ ህክምና ነበር የምከታተለው እዚህ መድሀኒቱን ማግኘት አልቻልኩኝም።  አይኔንም ያመኛል እና ህክምናውንም ሆነ መድሀኒቱን ማግኘት በፍፁም  አልቻልኩም። ፖሊሶቹ ሲይዙኝ በጣም ነበር የለመንኳቸው መድሀኒት እንድገዛ እነርሱ ግን እስርቤት ታገኛለሽ ብለው ከለከሉኝ ነገርግን እስከአሁን  ምንም ማግኘት አልቻልኩኝም ።”

በያዝነው የጎርጎሮሳውያኑ ወር መጀመሪያ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር  ዲና ሙፍቲ አፅንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት ‘ታላቁ  የኢትዩጵያውያን ወደ ሀገርቤት ጉዞ ጥሪው በመላው አለም ለሚኖሩ ዜጎችን ያካትታል ። አምባሳደሩ ጨምረው እንደተናገሩት በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ዜጎች አኗኗር ከግዜ ወደ ግዜ እያሽቆለቆለ ነው። ” ኢትዮጵያ ከእነዚህ ሀገራት የማያቋርጥ ግፊት እየደረሰባት ይገኛል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ችግር እየተባባሰ ስለመጣ መመርመር ይገባዋል ።” ብለዋል። አምባሳደሩ የመንግስትን ድክመት በተለይም በሳውድ አረቢያና የባህረ ሰላጤው ሀገሮች የሚገኙ ዜጎችን በተመለከተ አቅም ማጣትን እና ሀገሪቷ ላይ ያለውን የፀጥታ ችግር እንደ ምከንያት አሰቀምጠዋል።


“እኔ እና ልጄ እዚህ እስርቤት ከገባን ስምንት ወራት አለፈን። ” ይህንን ያለችው ከትግራይ ክልል ህይወቷን ለማሻሻል  ወደ ሳዉዲ አረቢያ  በባህር የተሰደደችው ዚያዳ ናት። ዚያዳ ጨምራም ” በቂ ምግብ እኔ ህክምና አናገኝም በተጨማሪም ክፍሉ ከአቅሙ በላይ ማለትም 200 በላይ ሴቶች በአንድ ክፍል ውስጥ በመኖራችን ህክምና በሌለበት እኔ እና ልጄ ለተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭ ሆነን ነው ያለነው።”

ዚያዳ እና ሌሎች ህይወታቸውን ለመለወጥ ወደ ሳውዲ አረቢያ በህገወጥም ሆነ በህጋዊ መንገድ የተጓዙ ሁሉ  የሚስማሙት የኢትዪጵያ መንግስት የዜጎቹን መጠበቅ ሲገባው በድፕሎማሲው ድክመት ሀላፊነቱን አለመወጣቱን ነው።

ነብዩ ሲራክ ጋዜጠኛ እና በሳውዲ አረቢያ ለረጅም ጊዜ የኖሩ እና በስደተኞች እና እስረኞች አያያዝ ላይ በመፃፍ እና ግንዛቤ በመፍጠር  የሚታወቁ የማህበረሰብ አንቂ ናቸው። ከእስረኞች እና ከቤተሰቦቻቸው የሚቀርቡ ከሰብአዊነት ያፈነገጡ የእስረኞች አያያዝ ወቀሳዋችን ላይ ነብዩ ይስማማል፤ ጨምሮ ሁኔታዋች የሚመስሉት በተለይም ኢትዪጵያውያን ላይ ለይቶ ማጥቃት እሰኪመሰል ይበረታል ይላል  ነብዪ ካየው ነገር በመነሳት። “ሁሉም የሚያዙት ህገወጥ ስደተኞች አይደሉም። እንዳንድ ጊዜ ህጋዊ የሆኑ ሰደተኞችን ምንም አይነት ማጣራት ሳያደርግ ፖሊስ ሰብሰቦ ያሰራቸዋል ለማረጋገጥ እንኳን አይፈልጉም ቆይቶ ተጣርቶ የሚወጡ ይኖራሉ የሚቆዩ እንዳሉ ሁሉ” በማለት ያስረዳል ።

 ነብዪ እንደሚለው ከሆነ ከግማሽ ሚልዪን በላይ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ ይኖራሉ። ከ እነርሱ ውስጥ ከ 100,000 በላይ ስደተኞች እስርቤቶች ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ። ከእስርቤት ውጭ  ወደ 200,000 የሚገመት ኢትዪጵያዊ ስደተኛ ለአደጋ ተጋልጠው ይገኛሉ።

እንደ ነብዪ ማብራሪያ ከሆነ  ከአንድ አመት የዘለለው የመንግስት እስረኞችን የመመለስ እንቅስቃሴ ከ 42,000 በላይ እስረኞችን መመለስ ቢችልም ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ባለመሰጠቱ  ችግሮች እየተባባሱ ነው። ” ነገር ግን በእስረኞቹ ሰብአዊ አያያዝ ላይ ለውጥ አላመጣም። ዛሬም ድረስ እሰረኞች እየተበደሉ እና ግፍ እየተፈፀመባቸው  እንዲሁም በብዛት ወደ እስርቤቶች እየተጋዙ ይገኛሉ” ይላል።

በህጋዊ መንገድ ወደ ሳዉዲ አረቢያ የገቡ ሰደተኞች ሳይቀር የእስራቱ ሰለባ ሆነዋል ። በአሁን ግዜ እስር ቤት የሚገኘው የአራት ልጆች አባት የሆነው የባህር ዳር ነዋሪ የነበረው አለሙ አንዱ ማሳያ ነው ።ከእስር ቤት ሆኖ ስላበት ሁኔታ ለአዲስ እስታንዳርድ ሲያሰረዳ “ላለፉት  ዘጠኝ ወራት ማነም ጅዳ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንሱል ሆነ ኤምባሲ ጎብኝቶን አያውቅም። እስካሁን ድረስ ያለነው ስንያዝ በነበርንበት ልብስ ነው ያለነው። እዚህ እስር ቤት ውስጥ ያለውን ግፍ እና ሰቃይ በቃላት መግለፅ አይቻልም ከሚነገረው በላይ የከፋ ነው ።” የቤተሰቡ የገቢ ምንጭ የነበረዉ አለሙ እንደሚለው ኑሮውን ለማሳካት በተሰደደበት ሀገር እስርቤት ውስጥ ስለገባ ሀገር ቤት ያለው ቤተሰቡ  በድህነት እየተሰቃዩ ናቸው። እኛ ምንፈልገው ሀገራችን መግባት ብቻ ነው ብሏል ካለበት የጅዳ አካባቢ እስርቤት።

ሌላው ምስክርነቱን ካለበት ሆኖ የሰጠን እና ቤተሰቡ እስርቤት እየማቀቁበት ያለው አህመድ በበኩሉ አሁን ባለው ሁኔታ ማንም ሰው ከስጋት እና አደጋ ነፃ አይደለም ይላል። ጨምሮም ሳውዲ በሚገኙ እስረኞች ጉዳይ የመንግስትን ቸልተኝነት ይወቅሳል። ” እኔ የኢትዪጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር በየሳምንቱ የሚያወጣውን መግለጫ እከታተላለሁ የሳውዲ ስደተኞችን በተመለከተ የሚናገሩት መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ አውነታ በፍፁም አያሳይም።” የሚለው አህመድ ” የሚያቀርቡት ሪፖርት ለፖለቲካ አላማ የሚውል የእስረኞቹን መሰረታዊ ሰብአዊ መብት ጥያቄዋች የማይመልስ ፣ ጥያቄዎች ከጋዜጠኞች ገፍተው ሲመጡ እስረኞችን ለመመለስ ስለሚደረጉ ጥረቶች ብቻ ነው በተደጋጋሚ የሚመልሱት” ሲል ተችቷል። 

“እኔ ህጋዊ ነዋሪ ነኝ ግን ከስጋት ነፃ አይደለሁም ። እህት እና ወንድሜ ሀገርቤት የየራሳቸው ቤተሰብ ያላቸው በእስርቤት ይገኛሉ። እንደ ቤተሰብ ለእነርሱ ምንም አይነት እርዳታ ማድረግም ሆነ መጠየቅ አልችልም።”  አህመድ ስለ ሁኔታዉ አስከፊነት ሲያሰረዳ።

አዲስ እስታንዳርድ በስልክ ያናገራቸው እስረኞች እንደገለፁት የሚያጠቡ እናቶች እና ልጆቻቸው  ነፍሰጡር ሴቶች እንዲሁም ህመምተኞች በአንድ ክፍል ውስጥ ያለ በቂ ምግብ ፣ ህክምና ፣ አልባሳት እና የመተኛ ቦታ ታጉረው ስለሚገኙ የኢትዮጵያ መንግስት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር በበኩሉ ባለፈው ሳምንት በነበረው  መደበኛ የመገናኛ ብዙሀን ሳምንታዊ መግለጫ ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረበለት ጥያቄ በቃል አቀባዮ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አማካኝነት መልስ ሰጥቷል። ” ከሳውዲ አረቢያ ዜጎችን የመመለስ እንቅሰቃሴ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት መንግስት ቅድሚያ በሰጣቸው ወቅታዊ ሌሎች ጉዳዩች ምክንያት ተቋርጦ ነበር። ነገርግን ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚሄድ የልኡካን ብድን ስላቋቋምን በቀጣይ ይሄ ቡድን ወደዛው ተጉዞ እስረኞችን ወደ ሀገራቸው ያስመልሳል” ብለው ነበር።

በዚህ ሳምንት በነበረው ሳምንታዊ መግለጫ አምባሳደር ዲና የልኡካን ቡድኑ ወደ ሳውድ አረቢያ ለመጓዝ ቪዛ እየጠበቁ እንደሆነ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል ። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.