እይታ፡- አፍሪካ እና ሩሲያ ዩክሬንን መውረር

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሶቺ ሩሲያ በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በምልአተ ጉባኤው ላይ ምስል በደቡብ አፍሪካ መንግስት

በማርክ ኤን ካትዝ

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 17 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡– አሜሪካ እና ምዕራባውያን አጋሮቿ ሩሲያን ዩክሬንን በመውረሯ አውግዘዋል። ነገር ግን አፍሪካን ጨምሮ በአብዛኛዎቹ ታዳጊ አገሮች ለሩሲያ ብዙ ርኅራኄ አሳይተዋል። የአፍሪካ መንግስታት እና የህዝብ አስተያየት ለሩሲያ ርኅራኄ እንዳላቸው የሚነገርበት አንዱ ምክንያት የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት አፍሪካን ከአውሮፓ ቅኝ አገዛዝ ነፃ እንድትወጣ እንዲሁም በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት በደቡብ አፍሪካ ከነበሩት ህዳጣን ነጮች አገዛዝ ነፃ መውጣቷን በመደገፍ ነው።

በዚህ ሳቢያ ብዙ አፍሪካውያን ከሩሲያ ጎን በመቆም ጸረ-ምዕራባውያን አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ሞስኮ አፍሪካውያን ከምዕራቡ ዓለም ጋር በነበራቸው ትግል ትደግፋቸው እንደነበረው ሁሉ በአሁኑ ሰዓት ብዙ አፍሪካውያንም ሩስያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ባጋጠማት ወቅታዊ ቀውስ አጋርነታቸውን እየገለፁ ነው።

ነገር ግን ይህ ስሜት በአፍሪካ ውስጥ የተስፋፋ ቢሆንም ከበስተጀርባ ባለው አመክንዮን ወጥ ያልሆነ አንድ ነገር አለ። የሩሲያ ዛር ስርወ-መንግስት የአውሮፓ ቅኝ ገዢ ነበረች። እንደ ብሪታንያ፣ ፈረንሣይ፣ ፖርቱጋል፣ ሆላንድ፣ ቤልጂየም እና ስፔን የባህር ማዶ የቅኝ ግዛቶችን ከገነቡበት በተለየ መንገድ፣ ሩሲያ በቅርበት ባሉ ሃገራት ላይ ግዛቷን አስፋፍታ ነበር።

የአውሮፓ ቅኝ ገዥ ኃያላን አውሮፓውያን ያልሆኑትን ሕዝቦችና ግዛቶች ድል አድርገው እንደገዙ ሁሉ፣ የሩሲያ የዛር መንግስት በማዕከላዊ እስያ፣ በካውካሰስ፣ በባልቲክ ክልል፣ በዩክሬን እና በሌሎችም ቦታዎች ያሉትን ጨምሮ ሩሲያዊ ያልሆኑትን ሕዝቦችና ግዛቶችን አሸንፋ ገዛታለች።

ምንም እንኳን ሁሉንም ባይሆን ከዛር ሩሲያ አስተዳደር ውድቀት በኋላ አዲሶቹ የኮሚኒስት ገዥዎች በቦልሼቪክ አብዮት እና በአንደኛው የዓለም ጦርነት የኋለኛው ዘመን ያጧቸውን አብዛኞቹን የሩሲያ ያልሆኑ ግዛቶችን መልሰው ያዙ። አዲሱ የሶቪየት አመራር የተለያዩ የሩሲያ ያልሆኑ ህዝቦች ብሄራዊ ስሜትን ለማረጋጋት በመሞከር ብዙ የሩሲያ ያልሆኑ ሪፐብሊኮችን ፈጠረ። እውነታው ግን እነዚህ የሩሲያ ያልሆኑ “ሪፐብሊኮች” በአፍሪካ እና በሌሎችም እንደነበሩት የተለያዩ “የሞግዚት አስተዳደሮች” የሩስያ ቅኝ ግዛቶች ነበሩ።

በመሰረቱ እንግዲህ፣ የአፍሪካ ቅኝ ገዢዎች አውሮፓውያን እንደነበሩ ሁሉ ሩሲያ የዩክሬን ቀኝ ገዥዋ ነበረች

እናም በአፍሪካ የሚገኙ የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች እና የሞግዚት አስተዳደሮች በነበረው ቅኝ አገዛዝ ደስተኛ በለመሆናቸው በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ነፃነታቸውን ለማስከበር ዕድሉን እንደተጠቀሙ ሁሉ፣ ዩክሬንን ጨምሮ የሩሲያ ቅኝ ግዛቶች በቀዝቃዛው ጦርነት መጨረሻ ነፃነታቸውን ለማረጋገጥ እድሉን ያገኙበት አጋጣሚ ተፈጠረ ።

በመሰረቱ እንግዲህ፣ የአፍሪካ ቅኝ ገዢዎች አውሮፓውያን እንደነበሩ ሁሉ ሩሲያ የዩክሬን ቀኝ ገዥዋ ነበረች። ፑቲን አሁን ዩክሬን ከህዝቧ የተወሰነ ክፍል ሩሲያዊ ነው በሚል አመክንዮ የሩሲያ አገዛዝ እንዲመለስ በመሻት በከፊል ወይም በሙሉ ዩክሬን ላይ እንደገና ለመቆጣጠር መፈለግ ብሪታንያ ወይም ሆላንድ ደቡብ አፍሪካን እንደገና ለመቆጣጠር ከሚፈልግ ጋር የሚያመሳስለው ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያሉት ህዳጣን ነጭ እንግሊዛዊ ወይም ደቾች የእንግሊዝ ወይም የደች አገዛዝ ይመለስልን እንደማለት ነው።

በተመሣሣይ ሁኔታ፣ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ሶቪየት የጥቁር ህዝብ ቁጥር አብላጫ ለነበራት አፍሪካ ለነፃነቷ ድጋፍ ስታደርግ እንደነበረው ሁሉ በአሁኑ ሰዓትም ምዕራባውያን በዩክሬን ለሚኖሩ አብላጫ ቁጥር ላላቸው ዩክሬናውያን ለነፃነታቸው ለሚያደርጉት ትግል የሚያደርጉት ድጋፍ ነው።

የአርታዒ ማስታወሻ: ማርክ ካትዝ በጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርሲቲ ሻር የፖሊሲ እና የመንግስት ትምህርት ቤት የመንግስት እና የፖለቲካ ፕሮፌሰር ሲሆኑ በአትላንቲክ ካውንስል ከፍተኛ ባልደረባ ናቸው።

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.