ዜና፡ በደቡብ ጎንደር ዞን በወረታ ከተማ በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ

በብሩክ አለሙ

ሰኔ15 ቀን፣2014 ዓ.ም፣አዲስአበባ፦በደቡብ ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ ማክሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም  ከቀኑ 10:00 ሰዓት አካባቢ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቤቶች ላይ  ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የወረታ ከተማ ኮሙኒኬሽን  አስታወቀ። 

በከተማው በጣለው ዝናብ  ቀበሌ 01 እስቴበርና እየሩሳሌም ሰፈር፣ ቀበሌ 01 እና 04 አሜሪካ ሰፈር እንዲሁም በተለምዶ እስላም መቃብር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያሉ በአዲስ ምሬት የተሰሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቤቶች ላይ የጣራ ቆርቆሯቸውን በመበሳሳት ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በአሁኑ ወቅት ሁሉም ነገር ውድ በሆነበት ጊዜ ቆርቆሮ  ገዝተው መስራት እንደማይችሉ ተናግረው መንግስትንና ማህበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል

የከተማው የአቅም ግንባታ ህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ቡድን በቦታው ተገኝቶ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የነጋገረ ሲሆን ለቡድኑ ማክሰኞ ሰኔ 13 2014 ዓ.ም በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት ባይኖርም በንብረት ላይ ግን ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰባቸው ገልዋል፡፡ አክለውም  በአሁኑ ወቅት ሁሉም ነገር ውድ በሆነበት ጊዜ ቆርቆሮ  ገዝተው መስራት እንደማይችሉ ተናግረው መንግስትንና ማህበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

የወረታ ከተማ አስተዳደር አመራሮችም በየቦታው እየተዘዋወሩ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎችና ተጎጅዎች የጎበኙ ሲሆን በህብረተሰቡ ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ በቆርቆሮ፣ ምስማር፣ የኘላስቲክ ልባስና በሌሎችም እቃዎች ላይ ነጋዴው የዋጋ ጭማሪ የሚያደርግ ከሆነ እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን ገልፀዋል።

በሰኔ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን በሰሜን ሜጫ ወረዳ ቆለላ ቀበሌ በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት ከ 1000 በላይ የአርሶአደር መኖሪያ ቤቶች ላይ  ሙሉ በሙሉ ውደሙት ማድረሱና  ከባድና ቀላል የንብረት ጉዳት መድረሱን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን  ቢሮ ማስታወቁ ይታወሳል።አስ

 

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.