አዲስ አበባ ታህሳስ 22፤ 2014፤ ከኤርትራውያን ቤተሰቦቹ ከአዲስ አበባ 45ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ የተወለደው አወጋዛቢው ደራሲ እና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረአብ ከ11 በላይ የመጀመሪያ መፅሐፍትን እና ሁለት አጫጭር ልብ ወለድ ለንባብ አብቅቷል።
ባለትዳር እና የ3 ልጀች አባት የነበረው ተስፋዬ ባሳለፍነው ሳምንት በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በህክምና ላይ እያለ በ53 አመቱ ህይወቱ አልፏል፡፡ ወንድሙ እንደተናረው ተስፋዬ ከኢትዮጵያ ወጥቶ በኬንያ፣ በደቡብ አፍሪካና በኔዘርላንድ ለብዙ ዓመታት ከቆየ በኋላ በቋሚነት ወደ ኤርትራ ተዛወሮ መኖር ጀምሮ ነበር ብሏል፡፡
ድርሰቶቹ አነጋጋሪ ቢሆኑም እንኳን በርካታ የስነ ፅሁፍ ባለሙያዎች የተስፋዬ ስራዎች የረቀቀ አጻጻፍ ስልቶች እንደሚታይባቸው ይመሰክራሉ ። በርካቶች የተስፋዬን የፈጠራ ችሎታ ቢተቹም አድናቂዎቹ ግን የተጨቆኑ ማህበረሰቦችን እዉነታ በስራዎቹ ማንፀባረቅ ችሏል ብለው ያመሰግኑታል።
ተስፋዬ በበኩሉ በተለይም አወዛጋቢ በሆነው የቡርቃ ዝምታ በተሰኘውን ስራውን ለሚቀርቡበት ትችቶች በአንድ ወቅት ባደረገው ቃለ መጠየቅ እንዲህ ሲል መልሷል፣ “በአማርኛ ስነ ጽሁፍ ታሪክ ሙሉ የኦሮሞ ስም ያላቸው ዋና ገጸ ባህሪያት ተጽፈው አያውቁም ፣ ጫላ እና ጫልቱ የሚሉ ስሞችም ለዘበኛ እና ለቤት ሰራተኛ መጠቀም ነበር የተለመደው። ” አክሎም “ከመነሻው የቡርቃ ዝምታን ለመጥላት በቂ መነሻዎች ነበሩ፣ ገና ሲጀመር እኔ ወያኔ ነኝ ፣ ከወያኔ ምን ይጠበቃል መከፋፈል ካልሆነ ተብሎ ይጀምራል፣ በመቀጠል ወላጆቼ ኤርትራውያን ናቸው እኔን ሻቢያ ብሎ ለመፈረጅ የወቅቱ ፋሽን ነበር” ሲል አስረድቷል ።
ተስፋዬ በኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስቴር የፕሬስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን የእፎይታ መጽሄትና ጋዜጦች ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል፡፡ ደራሲ እና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ደራሲያንና ጋዜጠኞች ስራዎቻቸውን ለማሳተም አስችሏል። ሁሉንም መጻህፍቶቹን በአማርኛ የጻፈ ሲሆን ጥቂቶቹ ወደ ትግርኛና በኦሮምኛ ተተርጉመው ለንባብ በቅተዋል ።
የደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረአብ የቀብር ሥነ ሥርዓት ትላንት ሀሙስ ዕኩለ ቀን ላይ በአስመራ ኻዝ ኻዝ መካነ መቃብር ቤተሰቦቹ፣ የጥበበ አድናቂዎችና ወዳጆቹ በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡ አስ