ትንተና፡ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ጦርነት ምክንያት ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት እና አስከፊ መዘዞቹ በኢትዮጵያ

በእቴነሽ አበራ

አዲስ አበባ ታህሳስ 23፤ 2014፤ ባለፈው አመት ህዳር ወር የተጀመረው የትግራይ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ1,300 በላይ የአስገድዶ መድፈር ድርጊቶች መከሰት ሪፖርት የተደረገ ሲሆን በህብረተሰቡ ዘንድ ባለው መገለል ሳቢያ በርካታ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በቡድን አስገድዶ መደፈር እና ተያያዥ ጉዳዮች ጨምሮ ሪፖርት ሳይደረጉ እንዳልቀሩ ብዙዎች ይከራከራሉ። 

እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በችግር እና በግጭት ወቅት በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንደሚጨምር የሚያመላክት ሲሆን የ2013 ዓም ጥናት እንደሚያሳየው  ከሦስት ሴቶች አንዷ በህይወት ዘመኗ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ደርሶባታል። ባለፈው ህዳር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ወቅት አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል ያሏቸውን የጋራ ምርመራ ይፋ አድርገዋል። ሁሉም ተዋጊ ሃይሎች የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሀይሎችን ጨምሮ ጾታን መሰረት ያደረጉ ወንጀሎችን በቡድን አስገድዶ መድፈር ጨምሮ በወጣት እና አረጋውያን ሴቶች ላይ  ሲፈፅሙ እንደነበር ዘገባው አመላክቷል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው አዲስ ዘገባ በአማራ ክልል ከነሀሴ 12 እስከ 21 ባለው ጊዜ ውስጥ 70 ሴቶች በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ታጣቂ ሃይሎች መደፈራቸውን ለክልሉ ባለስልጣናት ሪፖርት አድርገዋል። .

አዲስ ስታንዳርድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንፅፅር ትምህርትና የፖሊሲ ጥናቶች ማዕከል እጩ ዶክተር የሆኑት ሲያኔ አንለይን አነጋግሯል። እርሳቸው እንደገለፁት፣ “ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ማለት ሴት በሴትነቷ ወይም ወንድ በወንድነቱ ምክንያት የሚደርስባቸው ማንኛውም አይነት ጉዳት (አካላዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ወሲባዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ) ነው።ይህ አይነቱ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት በአለማቀፋዊም ሆነ በሀገርውሰጥ በምንከተለው አባታዊ ስረአት መዋቅር ምክንያት በልጃገረዶችና ሴቶች ላይ እየተባባሰ ይገኛል ” በማለት ተናግረዋል።

እጩ ዶክተሯዋ በመቀጠልም ፣ “የችግሩ ጥልቀት በተደራራቢ ችግሮች (ድህነት፣ የቤተሰብ ሁኔታ፣ ገጠር-ከተማ፣ ትምህርት፣ ወዘተ) እና በአካባቢያዊ ችግሮች ሲገናኙ ሊጨምር ይችላል።”  ሲያኔ ጨምረው ሲያሰረዱ በአለም ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፆታንመሰረት ያደረገ ጥቃት በጦርነት እና በግጭቶች ወቅት የሚባባስበት ሁኔታ እየጨመረ ሲሄድ የመከላከያ ስረአቱ እየተዳከመ ይሄዳል ምክንያቱም ያሉት ሀብቶች በሙሉ ወደ ግጭቱን ለማስተዳደር ይውላሉ። 

እንደ ኢትዮጵያ ባለ ግጭቶች እና ጦርነት እየተካሄደ ባለባቸው ሁኔታዋች ምንም እንኳን በበቂ ጥናት መደገፍ ቢገባውም ሁኔታዋች እንደሚያሳዪት ሴቶች የመጀመሪያ ተጎጂዎች ናቸው። አከለውም በየትኛውም አካል ቢፈፀሙም ” እነዚህ ድርጊቶች ከጦርነት መሳሪያዎች ጎራ ይካተታሉ።” 

ሲያኔ በመቀጠልም በተፈናቃዮች ጉዳይ እንኳን ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በታወቁ ወይም ባልታወቁ ግለሰቦች እና ቡድኖች እንደሚከሰት፣ የተፈናቃይ ካምፕ ሰራተኞችን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን እንደ መደለያ መጠቀም የተለመደ እንደሆነ አስረድተዋል።

አክለውም ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች እንደ ሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ እድሜ ጋብቻ ያሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እየጨመሩ ይሄዳሉ ምክንያቱም ወንጀለኞቹ የቤተሰብ አባላትን ያጠቃልላል እና አስተማማኝ የመረጃ መረብ አለመዘርጋቱ እንደ ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ፣ ፖሊስ እና የአካባቢ አስተዳደሮች ያሉ ተቋማትን ጨምሮ ለችግር የተጋለጡ ልጃገረዶችን ለመከላከል እየተባባሰ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በቂ አለመሆኑን ትናግራለች። 

እንደ ሲያኔ ገለጻ አብዛኞቹ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ሪፖርት ሳይደረጉ ይቆያሉ። እክለውም “በኢትዮጵያ ያለው ፆታን መሰረት ያደረገ ቀውስ በደንብ ያልተጠና፣ ያልተዘገበ ወይም በደንብ ያልተመዘገበ ነው። ይህ፣ በእኔ እምነት፣ የሪፖርቶቹ ዓላማ የተዛባ፣ ማን የበለጠ ጨካኝ እንደሆነ ማሳየት ላይ ያተኮረ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ዘገባዎች በሲያኔ አስተያየት ለፕሮፓጋንዳ መሳሪያነት ፍጆታ በመዋል ላይ ይገኛሉ። ” በሲቪል ማህበራት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የተዘገቡት ቁጥሮች የትኛው ወገን የበለጠ ጨካኝ እንደሆነ ለማሳየት.፣ በግጭቱ ውስጥ የተሳተፉ አካላት አንዳቸው ሌላኛውን ወንጀለኛ ለማድረግ ብቻ እየተጠቀሙበት ነው ። “

ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች የተረፉ ሰዎች ስለሚሰጡ የሕክምና ዘዴዎች ሲያስረዱም ባለድርሻ አካላትን የማሳተፍ አስፈላጊነት ላይ አጥብቀው ተናግረዋል ። አክለውም “በዚህ የአደጋ ጊዜ ሁኔታ ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና የማይተካ ነው ብዬ አምናለሁ። የአካባቢው ጤና ሰራተኞች የስነ-ልቦና እና የአካልዊ ጉዳቶች ፍላጎቶችን ፣ወሲባዊ እና ስነ ተዋልዶ ጤና እና መብቶችን ሌሎች አገልግሎቶችን ጨምሮ እንዲያገኙ ማስቻል ወሳኝ ነው። የሚታየውን (አካላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ) እና የማይታዩ (ከአደጋ በኋላ ያለ የመንፈስ ጭንቀት) የጥቃት ቁስሎችን ለመፈወስ፣  ህብረተሰቡ የሚደግፈው እና በባለሙያዎች በሚመራ ህክምና አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ተሞክሮው በሌሎች ሀገሮች ውጤታማ ስለሆነ። ትምህርት ቤቶች በጦርነት እና በስደት የደረሰባቸውን ጉዳት በጨዋታ፣ በምክር እና ለልጆች ተስማሚ በሆነ የትምህርት ቤት አከባቢዎች ውስጥ ያጋጠሙትን ልጆች ለማከም ምቹ ቦታ ናቸው” ብለዋል።

ነገር ግን ሲያኔ ከመጀመሪያውም ጀምሮ፣ ወጣት ወንድ እና ሴት ልጆችን ስለ ጾታ እኩልነት፣ ስምምነት፣ መከባበር እና ልዩነትን በቤት እና በትምህርት ቤት ማስተማር ከሁሉም በላይ አስፈላጊ እንደሆነ ታስባለች። ጨምራም “ትምህርት ቤቶችን ለሴቶችና ለወንዶች ልጆች ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ እንዲሆኑ ማስቻል፣ የፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ሪፖርት አቀራረብ ስርዓትን ማበረታታት፣ ትምህርት ቤቶችን ከጤና እና የህግ አገልግሎቶች ጋር ማስተሳሰር፣ ከመገናኛ ብዙኃን እና ከማህበራዊ ሚዲያ ሰለ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ ጥብቅና እንዲቆሙ ግፊት ማድረግ፣ የወንዶችን ተሳትፎ  ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ተግባር ላይ ማሳደግ  የሴቶች ማህበራትን መገንባት እና ማጠናከር፣  የሴቶች ክለቦች መብቶቻቸው ለመብታቸው እንዲሟገቱ. ማጠናከር” መፍትሄ ይሆናልሲሉ ያስረዳሉ።

በመጨረሻም  ሲያኔ መሰል ችግሮችን ወደፊት ለመፍታት “በችግር ጊዜ፣ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንደ ዋና የአደጋ ጊዜ ምላሽ ቦታ መስጠትን ጨምሮ፣ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች  ላይ በጦርነት፣ በግጭት እና በስደት አውድ ላይ የተደረጉ ጥናቶችን መደገፍ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ጉዳዮችን ለመፍታት ረጅም መንገድ ይጠቅማል” ብለው አጠናቀዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.