አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 – የቀድሞ የ”ኢትዮ ፎረም” አዘጋጅ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ዛሬ ማለዳ ከግምቱ 1 ሰዓት አካባቢ አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ አካላት መወሰዱን ጠበቃው ታደለ ገ/መድህን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።
ጠበቃው አያይዘውም “ወዴት እንደወሰዱት አላውቅም። የት እንዳለ እያፈላለኩት ነው” ብለዋል።
‘ኢትዮ ፎረም’ የተሰኘው የዩትዩብ መገናኛ ብዙኀን አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስን ሃሙስ ግንቦት 18፣ 2014 ዓ. ም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ስር ያዋለው ሲሆን ግንቦት 19 ቀን ጋዜጠኛውን ፍርድ ቤት አቅርቦ “ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት” ጠርጥሬዋልሁ ሲል ገልጾ እንደነበር ይታወሳል።
በወቅቱ በነበረውም ክርክር የተከሳሽ ጠበቃ ታደለ ገብረ መድህን በበኩሉ ደንበኛቸው ላይ የቀረበው ምርመራ ግልፅነት የጎደለው መሆኑን ጠቅሰው ፍርድ ቤቱ ደንበኛቸውን በዋስ እንዲለቀቅ ጠይቀው ነበር።
ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በሰጠው የ10,000 ብር የዋስትና መብት ከእስር በፈታቱ ይታወሳል። አስ