በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞኖች ምን ተፈጠረ?

በደረጀ ጎንፋ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2014 – በኦሮሞ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች በአዲስ መልክ በተቀሰቀሰው ግጭት 10 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በርካታ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለፀ። የኦሮሞ ልዩ ዞን የጅሌ ዱሙጋ ወረዳ ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ፤ እሑድ ሚያዝያ 9 ቀን ከሰአት በኋላ ግጭት መቀስቀሱን ተናግረዋል።

ከበደ (ስማቸው ለደህንነት ሲባል የተቀየረ) የጅሌ ዱሙጋ ከተማ ነዋሪ ሲሆን ኮላሽ ከሚባል ግጭት ካለበት አካባቢ አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረው ሲሆን አካባቢው በሸዋ ሮቢት (ሰሜን ሸዋ ዞን) እና በወሰን ቁርቁር (የኦሮሞ ልዩ ዞን) መካከል ያለ ድንበር ነው ሲል ተናግረዋል። እንደ እርሱ ገለጻ፣ ፋኖ እሁድ አመሻሽ 11፡00 ላይ በነዋሪዎች ላይ ጥቃት ከፍቷል።

አክሎም “ፋኖ ራሱን አደራጅቶ የኮከብ ምልክት የሌለውን አረንጓዴ ቢጫ፣ ቀይ ባንዲራ በመያዝ ወደ ኦሮሞ ልዩ ዞን በመግባት በነዋሪዎች ላይ ተኩስ በመክፈት ሁለት ገበሬዎችን ገድሎ በርካቶችን አቁስሏል።  የመንግስት የፀጥታ ሃይል  ጣልቃ ከገቡ በኋላ ግጭቱ ጋብ ያለ ቢሆንም፤ “ፋኖ ሌሊቱን ተቀናጀቶ እንደገና ጥቃት ፈፅሟል ግጭቱም ሰኞ ቀኑን ሙሉ ሲካሄድ ውሏል” ሲል ተናግሯል።

ግጭቱ ከአካባቢው የጸጥታ ሃይሎች አቅም በላይ በመሆኑ፣ የፌደራል ፖሊስና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጣልቃ እንዲገባ ተጠይቋልም ብሏል።

“በኔ ፊት አንድ ሰው ተገሏል፣ ሌሎች ሶስት ሰዎች ሲሞቱ አይቻለሁ፣ ብዙዎችም ቆስለዋል እነዚህ እኔ ያየኋቸው ብቻ ናቸው ሌሎች ብዙ ይኖሩ ይሆናል” ያለው ከበደ፣ ታጣቂዎቹ የኦሮሞ ልዩ ዞን መኖር የለበትም የሚል እምነት ነው ያላቸው” ሲልም ተናግሯል።

የሸዋ ሮቢት ከተማ ነዋሪ የሆነው አንተነህ ተካ በአማራ ልዩ ሃይል እና በፋኖ መካከል ግጭት መፈጠሩን ለአዲስ ስታንዳርድ የተናገሩ ሲሆን፣ አክለውም “ፋኖው ከልዩ ሃይሉ ድጋፍ ይጠብቅ ነበር። ልዩ ሃይሉ ግን ፈቃደኛ ባለመሆኑ ግጭት ተፈጥሯል” ሲል አብራርቷል። አያይዘውም የሸዋ ሮቢት ነዋሪዎች ወደ ደብረ ሲና እና ደብረ ብርሃን ከተሞች መሸሻቸውን ገልጸዋል።

የጂሌ ዱሙጋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አህመድ መሀመድ ትናንት በስልክ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት የክልሉ ልዩ ሃይል እና የፌደራል የጸጥታ ሃይሎች ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር በመተባበር ግጭቱን መቆጣጠር ችለዋል። አስተዳዳሪው የክልሉ ልዩ ሃይል ጣልቃ ለመግባት ባደረገው ሙከራ ፋኖ ከልዩ ሃይሉ ጋር መጋጨቱንም አብራርቷል። ፋኖ ግጭት ለመቀስቀስ ህዝቡን እያዋከበ ነው፣ ግጭት እየፈጠረ ነው ሲሉም ወንጅሏል።

አስተዳደሩ ግጭቱ ለምን እንደተነሳና የሟቾችን ቁጥር ለማወቅም ባሰባሰቡት መረጃ  መሰረት የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 34 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

የወረዳው ሌላኛው ነዋሪ አቶ ፋንታሁን (ስማቸው የተቀየረ) ለአዲስ ስታንዳርድ ጥቃቱ ከጂሌ ዱሙጋና  በባቲ ከተማ ዙሪያ በሁለት አቅጣጫዎች መከፈቱን አስታውሷል። “ህዝቡ ቀዬውን ጥሎ ላለመሰደድ አጸፋውን መልሷል። ሰኞ ጧት ከፍተኛ ጦርነት ነበር የተካሄደው” ያሉው አቶ ፋንታሁን በኦሮሞ ልዩ ዞን ነዋሪዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ጠቅሰው “አሁን ለማፈናቀል፣ሰዎችን መግደል እና ማሰቃየት ግልፅ ጦርነት ከፍተዋል” ብሏል።

አቶ ፋንታሁን አክለውም  በትላንትናው እለት ረፋድ ላይ የፌደራል ፖሊሶች ወደ አካባቢው ገብተው ሰላም መፈጠሩን ተናግረዋል። ስለ ዛሬው ሁኔታ ሲናገሩ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን እና ውጊያው ቢቆምም ውጥረቱ እየጨመረ መሆኑን አስረድተዋል።

ሌላ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሸዋ ሮቢት ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ነዋሪዎቹ ግጭቱ እንደ አሁን ቀደም ወደ ከተማዋ ከመድረሱ በፊት መሰደድ መጀመራቸውን አስረድተዋል። የከተማው አስተዳደር ነዋሪዎች እንዳይሰደዱ ለማስቆም ቢሞክርም ህዝቡን መቆጣጠር አልቻሉም ያለው ነዋሪው ዛሬ ግን ግጭቱ ከተረጋጋ በኋላ ሰዎቹ ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው ብሏል። የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ጋብራን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.