በማህሌት ፋሲል
አዲስ አበባ፡ ሰኔ 22/2013-የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር እና የህገመንግስት ጉዳዩች ችሎት በነ ጃዋር መሀመድ መዝገብ የተከሰሱትን ጃዋር መሀመድ በቀለ ገርባ ሀምዛ አዳነ እና ደጀኔ ጣፋ ለሁተኛ ግዜ ካሉበት ማረሚያ ቤት ችሎት አንቀርብም በማለታቸው ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ትእዛዝ ሰጠ፡፡
ተከሳሾቹ የፍርድ ቤት ትእዛዝ በአስፈጻሚ አካለት እየተከበረ ስላስሆነ ከዚበውሀላ ችሎት አንቀርብም በማለት ለችሎቱ የፅሁፍ የገለፁ ሲሆን ችሎቱም በቀጣይ ቀጠሮ ማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በቀጣይ ቀጠሮ ተከሳሾችን እንዲያቀርብ ትእዛዝ ቢሰጥም ተከሳሾቹ በድጋሚ ሳይቀርቡ በመቅረታቸው ችሎቱ ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ወስኗል፡፡
ፍርድ ቤቱ በኢትዩጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 20ን በመጥቀስ በችሎት ለመቅረብ ፈቃደኛ ያልሆኑት አራት ተከሳሾች ጉዳቸው በሌሉበት እንዲታይ ተለዋጭ ቀጠሮ ለሀምሌ 30 2013 ሰቷል፡፡ AS