ዜና፡-በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠሩ ሶስት ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ

በማህሌት ፋሲል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27 2013-የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብር እና ህገ መንግስት ጉዳዩች ችሎት የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥረው የነበሩ 3 ተከሳሾች ላይ ከእድሜ ልክ እስከ ስድስት ወር እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጠ፡፡
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ገሏል የተባለው አንደኛ ተከሳሽ ጥላሁን ያሚ ጥፈተኛ በተባለበት ፀረ ሽብር አዋጅን 1176/2012 አንቀፅ 3 በመተላለፍ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ችሎቱ ወሰነ ፡፡
በግድያው ተባብሯል የተባለው ሁለተኛ ተከሳሽ ከበደ ገመቹ የወንጀለኛ ህጉን 540 በመተላለፍ የ 18 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ትእዛዝ ተሰቷል፡፡
ሶስተኛ ተከሳሽ አብዲ አለማየሁ ጥፋተኛ በተባለ በ 443/1 የወንጀል ህጉን በተላለፍ እጁ ከተያዘበት ግዜ የሚቆጠር በስድስት ወር ቀላስ እስራት እንዲቀጣ ፍርድቤቱ ውሳኔ ሰቷል፡፡
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሰኔ 22 2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ በሽጉጥ ተመቶ ህይወቱ ማለፉይታወሳል፡፡

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.