ዜና: የሀረሪ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ጋዜጠኛ እና አርታኢ በዋስ ተፈታ

በእቴነሽ አበራ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12/2014 –  በሀረሪ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ የአፋን ኦሮሞ አርታኢ  እና ጋዜጠኛ ሙሃይዲን አብዱላሂ ከዘጠኝ የእስር ቀናት በኋላ በ በዋስ ተለቀቀ። ሙሃይዲን ‘እውነትን በመዘገቡ ምክንያት’ ማስፈራሪያ ይደርሰዉ እንደነበር እና ይህም ለመታሰሩ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ለአዲሰ ስታንዳርድ ተናግሯል ። 

በተለይም በቅርቡ ጎንደር ላይ የተፈጠረውን  ችግር አስመልክቶ መፍትሔ የሚሰጥ ጠንካራ መጅሊስ ያስፈልገናል በማለት በፌስቡክ ገፁ የፃፈው ፅሁፍ ለእስራት እንዳበቃው አስረድቶል። 

” የፖሊስ መርማሪዎች አና አቃቤ ህግ የሁለት ሺህ ብር ዋስ አቅርቤ ከመለቀቄ በፊት ቢሮቸው ጠርተው አስፈራርተውኛል። በፌስቡክ ገፄ መፃፌን እንዳቆም አሳስበውኛል። ቃል በቃልም ለራስም ሆነ ለቤተሰብህ ስትል መፃፍህን አቁም ካልሆነ ወደ እስርቤት እንደምትመለስ እወቅ ብለውኛል” ብሏል ሙሀይዲን። 

ሙሃዲን አክሎ እንደተናገረው በሙያው እንዲ ያሉ  ችግሮች ሲያጋጥመው ይህ የመጀመሪያው አይደለም። “ባለፈው አመት ባልታወቀ ምክንያት የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት የስራ ባልደረቦቼና ጓደኞቼ  ባሉበት ድብደባ ደርሶብኛል። የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የሚመለከተው አካል በጉዳዩ ላይ የልዩ ሃይል አባላትን እንዲከሱ ብጠይቅም ስለ ጉዳዩ ምንም እንደማያውቁ ነግረው መልሰውኛል“ ሲል አውስቷል።

እንደ ጋዜጠኛው ገለፃ የእስር ትዕዛዙ ከታሰረ በኋላ እንደተሰጠውም ገልጿል። ፍርድ ቤት ለምርመራ የ14 ቀናት መስጠቱ ይታወሳል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.