ዜና፡ በሊባኖስ እና በኢትዮጵያ መካከል የሰራተኛ ቅጥርን በተመለከተ የተደረሰው ስምምነት ለቤት ሰራተኞች መብት የሚሰጠው ከለላ አነስተኛ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13/2015 ዓ.ም፡- በሊባኖስ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ከሰራተኛ ቅጥር እና መብት ጋር በተያያዘ የተደረሰው ስምምነት ለቤት ሰራተኞች የሚሰጠው የመብት ከለላ አነስተኛ መሆኑን ሚድል ኢስት አይ የተሰኘ ድረገጽ ዘገባ አጋለጠ። ድረገጹ ተመልክቸዋለሁ ያለው የሁለቱ መንግስታት የስምምነት ሰነድ ላይ ምንም አይነት የዝቅተኛ የቅጥር ደመወዝ እንዳልተቀመጠ