ዜና፡ በሊባኖስ እና በኢትዮጵያ መካከል የሰራተኛ ቅጥርን በተመለከተ የተደረሰው ስምምነት ለቤት ሰራተኞች መብት የሚሰጠው ከለላ አነስተኛ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13/2015 ዓ.ም፡- በሊባኖስ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ከሰራተኛ ቅጥር እና መብት ጋር በተያያዘ የተደረሰው ስምምነት ለቤት ሰራተኞች የሚሰጠው የመብት ከለላ አነስተኛ መሆኑን ሚድል ኢስት አይ የተሰኘ ድረገጽ ዘገባ አጋለጠ።

ድረገጹ ተመልክቸዋለሁ ያለው የሁለቱ መንግስታት የስምምነት ሰነድ ላይ ምንም አይነት የዝቅተኛ የቅጥር ደመወዝ እንዳልተቀመጠ ተገልጿል። በተጨማሪም የሊባኖስ አሰሪዎች የሚቀጥሯቸውን ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ፓስፖርት በመያዣነት ሊወስዱና በቤታቸው ማስቀመጥን የሚችሉበት የህግ አግባብ መቀመጡን ድረገጹ በዘገባው አስታውቋል።

በሊባኖስ መንግስት እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል በሚያዚያ ወር የተደረሰው ስምምነት ለህዝብ ይፋ አለመደረጉን የጠቆመው ዘገባው ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መገናኛ ብዙሃን አወንታዊ ይዘት ያለው ከፍተኛ ሽፋን አግኝቶ እንደነበር አውስቷል። ከመገናኛ ብዙሃኑ ሽፋን ባለፈ የኢትዮጵያ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈርያት ከሚል በማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ፌስቡክ ገጻቸው ስምምነቱን አስመልክተው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤

ከስምምነቱ ዋና ዋና ይዘቶች መካከል ቀድሞ የነበረውን ደመወዝ ትርጉም ባለው ደረጃ ያሻሻለ፣ የመንቀሳቀስ፣ የጉዞ ሰነድ የመያዝ መብት፣ የዓመት ዕረፍት፣ ህክምና (የኢንሹራንስ ሽፋን)፣ ከቤተሰብ ጋር የመገናኘት እንዲሁም ከሌሎች ሀገራት ዜጎች አንፃር መድልኦ የሌለው ጥቅም፣ ክብርና ጥበቃን የተመለከቱ መብቶች ይገኙበታል ማለታቸውን አውስቷል።

12 ገጽ የሚሆነው የስምምነቱ ሰነድ እና የሰራተኞችን ቅጥር አስመልክቶ የሚያትተው ስምንት ገጽ ሰነድ የሰራተኞችን መብት በማስጠበቅ ረገድ የሚኖረው ሚና አጠራጣሪ መሆኑን ያሳያል ሲል ድረገጹ በዘገባው አመላክቷል። ስምምነቱ ምንም አይነት የዝቅተኛ ዋጋ ተመን ካለማስቀመጡም ባሻገር የሚፈጸሙት ስምምነቶች በሊባኖስ ህግ መሰረት ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው ተጠቁሟል፤ የሌባኖስ ህግ በስደተኛ ሰራተኞች ላይ ተግባራዊ እንዲደረግ እንደማያስገድድ ድረገጹ አመላክቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ያጋጠመውን የውጭ ምንዛሬ ብቻ ታሳቢ በማድረግ እና በውጭ የሚገኙ ዜጎቹ በሐዋላ አማካኝነት የሚላክን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ሲል የዜጎቹን መብት በማስጠበቅ ረገድ ትኩረት አልሰጠም ሲል ድረገጹ በዘገባው ተችቷል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.