ዜና፡ በመንግስትና በቅዱስ ሲኖደስ መካከል የቃላት ጦርነት ተባብሶ ቀጥሏል፤ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ–ኃይል ሰልፍ እናዳይካሄድ ቢያስጠነቅቅም ሲኖዶሱ ሰላማዊ ሰልፉ ተፈጻሚ እንደሚሆን ገልጧል
አዲስ አበባ፣ የካቲት፣3/ 2015 ዓ.ም ፡- በመንግሥትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየተባባሰ በሄደበት ወቅት ሁለቱም ተቋማት ትላንት ከስዓት በኋላ የራሳቸውን አቋም የሚያንጸባርቅ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ መንግስት በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው "መንግስትን በትጥቅ ሃይል ለመነቅነቅ" እየሰሩ