ዜና ትንታኔ: በአማራ ክልል የፀጥታ መዋቅሩ በትግራይ ሃይሎች የሚሰነዘር ጥቃት፣ ስርዓት አልበኝነት እና ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ለመግታት ዝግጁ እንዲሆን ተጠየቀ
አዲስ አበባ ግንቦት 6፣ 2014 ፦ የአማራ ክልል የጸጥታው ምክር ቤት በክልሉ ያለውን ሰላምና ጸጥታ ሁኔታ መገምገሙን ገልጾ የጸጥታ መዋቅሩና የክልሉ ህዝብ "በአማራ ክልል ላይ ዳግም ጦርነት አውጀዋል" ባላቸው የትግራይ ሃይሎች የተቃጣበትን ወታደራዊ ጥቃት ለመከላከል እንዲዘጋጅ አሳስቧል። ምክር ቤቱ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ አደጋ ላይ የሚጥሉና የክልሉን