ፈጠራ: ቪዛ በኢትዮጵያ የፊንቴክ ጀማሪዎችን እና ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ የሚያስችለውን አዲስ ፕሮግራም ጀመረ

የመካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ፣ እንዲሁም የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ክልል የቪዛ ፕሬዝዳንት አንድሪው ቶሬ የቪዛን ቁርጠኝነት በኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያዎችን ለማስፋት ከመንግስት እና ከፋይናንሺያል ስነ-ምህዳሩ ጋር በቅርበት ስራዎች እንደሚሰሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2015 ዓ.ም – ቪዛ የፊንቴክ ፈጠራን ለማራመድ እና በሴቶች የሚመሩ አነስተኛና መካከለኛ ንግዶችን ለመደገፍ ሁለት አዳዲስ ውጥኖችን በማወጅ ዲጂታል ክፍያዎችን በኢትዮጵያ ለማስፋት ያለውን ቁርጠኝነት አጠናክሮ ቀጥሏል። የመካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ እንዲሁም የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ክልል የቪዛ ፕሬዝዳንት አንድሪው ቶሬ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ቪዛ ለሁለተኛ ጊዜ ”ቪዛ በየትኛውም ቦታ (VEI)” የተሰኘውን ተነሳሽነቱን ለማጠናከር የፊንቴክ ውድድር ለማካሄድ እና “ቀጣይ እሷ ናት” የሚለውን የሴቶች ማጎልበቻ እንቅስቃሴ ለመጀመር ማቀዱን ይፋ አድርጓል። .

በ”ቪዛ በየትኛውም ቦታ (VEI)” በኩል፣ መጪውን የክፍያ ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚያስችሉ ፈጠራዎችን እንዲያካፍሉ ቪዛ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የፊንቴክ ስራ ፈጣሪዎችን ለስራ የሚጋብዝ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2021 አሪፍፔይ፣ የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሽያጭ የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር የመጀመሪያ በመሆን የVEI ኢትዮጵያ ውድድርን አሸንፏል። እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ፣ VEI ከ100 በላይ አገሮች ለተውጣጡ ስራ ጀማሪዎች ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

የቪዛ “ቀጣይ እሷ ናት” ፕሮግራም የሴቶች ንብረት የሆኑ አነስተኛ ንግዶችን በገንዘብ፣ በስልጠና እና በአማካሪነት የሚደግፍ አለም አቀፍ ፕሮግራም ነው። እ.ኤ.አ ከ2020 ጀምሮ ቪዛ ከ250 በሚበልጡ የገንዘብ ድጋፎች እና በሴቶች ባለቤትነት ስር ያሉ የንግድ ተቋማትን በማሰልጠን ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት አድርጓል።

እ.ኤ.አ ከመጋቢት 2020 ጀምሮ በአዲስ አበባ ውስጥ እንቅስቃሴ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ቪዛ የዲጂታል ንግድ እና የገንዘብ እንቅስቃሴን ለተጠቃሚዎች፣ ነጋዴዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት እና የመንግስት አጋሮች ልዩ እድሎችን በመፍጠር በፋይናንሺያል ስነ-ምህዳር ላይ እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያ የ2025 የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂን በ2020 የጀመረች ሲሆን አላማውም ዲጂታል እና ፋይናንሺያል አካታች ኢኮኖሚን በመለወጥ እና በማሳደግ በ2025 ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት እስከ 39 በመቶ ድርሻ እንድታበረክት ይጠበቃል።

የመካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ እንዲሁም የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ክልል የቪዛ ፕሬዝዳንት አንድሪው ቶሬ እንዳሉት፡ “ቪዛ በኢትዮጵያ ያለውን የክፍያ ስነ-ምህዳር ለማጠናከር ቁርጠኛ ነው፣ በዚህም መሰረት ከ2020 ጀምሮ እውነተኛ እድገትን በመገንባት ዲጂታል ክፍያዎችን ለማስፋት ከአጋር አካላት ጋር እየሰራ ነው። ፊንቴክስ እና በሴቶች የሚመሩ አነስተኛ ንግዶች የኢኮኖሚ እድገትን በማፋጠን ላይ የሚጫወቱትን ጠቃሚ ሚና ተገንዝበናል፣ በዚህም መሰረት የዲጂታል ዘመንን ለማበልጸግ የሚረዱ አስፈላጊ የሆኑ መሳሪያዎችን እና ግብዓቶችን የሚያቀርቡ አለምአቀፍ ፕሮግራሞችን ማቅረብ በመቻላችን ደስተኞች ነን።

የቪዛ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ኃላፊ የሆኑት አይዳ ዲያራ በበኩላቸው “የቪዛን አለም አቀፍ ፕሮግራሞች ወደ ኢትዮጵያ በማምጣታችን ኩራት ይሰማናል። በቀጣይነት በዲጂታል ኢኮኖሚ እና በአጠቃላይ የጀማሪዎች ተሳትፎን በማጠናከር ላይ ነን። VEI እና She’s Next የፋይናንሺያል ማካተትን ለማስፋት በመርዳት ረገድ ያደረጉትን ስኬት እና ተፅእኖ አይተናል ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ ሸማቾች እና ነጋዴዎች የሚከፍሉበት እና የሚከፈልበት ምርጥ መንገድ ለማቅረብ ለመስራት የምናደርገውን ጉዞ እንድናፋጥን ያደርጋል” ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት ቪዛ የአፍሪካን ተስፋፊ ጅምር ማህበረሰብ በሙያ፣ በግንኙነቶች እና በኢንቨስትመንት ፈንድ ለማስቻል የሚረዳውን አዲሱ የቪዛ አፍሪካ ፊንቴክ አክስሌሬተር ፕሮግራም መጀመሩን ማስታወቁ ይታወሳል።

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.