ዜና፡ የእንግሊዝ ሮያል ኢንጂነሪንግ አካዳሚ ኢትዮጵያዊው መሐንዲስን ጨምሮ 15 አፍሪካዊያንን እ.ኤ.አ. ለ2023 ዓም የአፍሪካ ምህንድስና ፈጠራ ሽልማት እጩ አድርጎ መረጠ

ፍቅሩ ገብረ ድንቁምባብ: ፎቶ- በአማኑኤል ስለሺ ለእንግሊዝ ሮያል አካዳሚ ኢንጂነሪንግ


አዲስ አበባ፣ ህዳር 14/ 2015 ዓ.ም፡- የእንግሊዝ ሮያል አካዳሚ ኢንጂነሪንግ እ.ኤ.አ. ለ2023 ዓ.ም. የአፍሪካ ምህንድስና ፈጠራ ሽልማት ኢትዮጵያዊው ሜካኒካል መሀንዲስ ፍቅሩ ገብረ ድንቁምባብን ጨምሮ  15 እጩ ተወዳዳሪ አፍሪካውያን የስራ ፈጣሪዎች  ዝርዝር አስታወቀ።

ፍቅሩ ገብረ ዲኩምባብ በፈጠረው  ሁለገብ የአፈር ጡብ ማሽን በእጩነት መዝገብ ውስጥ መስፈሩን አካዳሚው ባወጣው መግለጫ ጠቁሟ፡፡ እንደ አካዳሚው መግለጫ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ፈጠራዎች ለተባበሩት መንግስታት ዘላቂ ልማት ግቦች ወሳኝ የምህንድስና መፍትሄዎችን ይሰጣሉ ተብለው የታመነባቸው ናቸው። መግለጫው አያይዞም ፈጠራዎቹ  የውሃ, የጤና አጠባበቅ, ግብርና, ትምህርት, የምግብ ዋስትና እና የኢነርጂ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያግዙ  ናቸው።

ከ15ቱ ተወዳዳሪዎች  አሸናፊ ለሚሆነው ተወዳዳሪ  25,000 ፓውንድ ሽልማት የሚበረከትለት ሲሆን ለሦስት ለፍጻሜ የደረሱት ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 10,000 ፓውንድ ሽልማት እንደዚሁም በውድድሩ ላይ ከፍተኛ ተስፋ ሰጭ ፈጣሪ ለሆነ አንድ ተወዳዳሪ  5,000 ፓውን ሽልማት ይሰጠዋል ።

እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓም በእንግሊዝ  ሮያል ኢንጂነሪንግ አካዳሚ የተመሰረተው  አፍሪካ የምህንድስና ፈጠራ ሽልማት ከተመሰረተበት ግዜ ጀምሮ ለአፍሪካ እና ለአለም አቀፍ ተግዳሮቶች በሀገር ውስጥም ሆነ ከዚያ ባለፈ ሊያገለግል የሚችሉ መፍትሄዎችን ለሚፈጥሩ ተስፋ ላላቸው አፍሪካውያን እየሸለመ ነው።

ሮያል ኢንጂነሪንግ አካዳሚ ይህንኑ የአፍሪካ ትልቁ ሽልማት የኢያስገኘውን ለዘጠነኛ ዓመቱ ከአንጎላ፣ ካሜሩን፣ ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ እና ዚምባብዌ የተውጣጡ አህጉራዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ አስተዋፅዖ ያደረጉ 15 ጥሩ ስራ ፈጣሪዎችን አስመዝግቧል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተገለፀው ለዚህ ሽልማት የሚመረጡት ፈጣሪዎች ለየት ያለ የድጋፍ ፓኬጅ የንግድ ኢንኩቤሽን፣ መካሪ፣ የገንዘብ ማሰባሰብያ እና ግንኙነት እንዲሁም በአለም አቀፍ ትስስር ከፍተኛ ደረጃና ልምድ ያላቸው በእንግሊዝ እና በአፍሪካ የሚገኙ መሐንዲሶች እና የንግድ ባለሙያዎችን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል። 

የአፍሪካ ምህንድስና ፈጠራ ሽልማት  በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል  ተብሎ የሚገመት ሲሆን ሲሆን እስካሁን  3 ሺ 5 መቶ 85 የስራ እድል የፈጠረ ከዚህ ውስጥ 1 ሺ 7 መቶ 66 ለሴቶች እና 2 መቶ 11 ለአካል ጉዳተኞች መሆኑንም በመግለጫው ተመልክቷል።  አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.