ዜና፡ የአለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የሚያቀርበውን የምግብ እርዳታ ማቆሙን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3/2015 ዓ.ም፡- እንደ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ ሁሉ የአለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሲያቀርብ የነበረውን እርዳታ በተለያዩ መንገዶች ላልታለመለት አላማ እየዋለ ነው በሚል ላልተወሰ ግዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙሉ በሙሉ ማቆሙን አስታወቀ።

በኢትዮጵ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተጎጂዎች ተብሎ የሚቀርብ እርዳታ ላልታለመለት አላማ እየዋለ መሆኑ በመረጋገጡ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በኢትዮጵያ የሚያካሂደውን የእርዳታ አቅርቦት ማቋረጡን ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው የኢሜይል መልዕክት ማታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለም የምግብ ፕሮግራም ትላንት ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም አመሻሽ ላይ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ለተረጂ ወገኖች የሚያቀርበው እርዳታ በተለያዩ መንገዶች ላልታለመለት አላማ እየዋለ መሆኑን ገልጿል።

የምግብ እርዳታ ለተጎጂዎች እንዲዳረስ ከማድረግ ውጭ ለልታለመለት አላማ መዋሉ ፍጹም ተቀባይነት የለውም ሲሉ የገለጹት የፕሮግራሙ ዋና ዳይሬክተር ሲንዲ ማኬይን የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊቱ ፈጻሚዎችን ለመመርመር እና ተጠያቂ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን እናደንቃለን ብለዋል።

120 ሚሊየን ቁጥር ያለው ህዝብ ከሚኖርባት ኢትዮጵያ 20 ሚሊየን የሚሆነው የምግብ እርዳታ ጠብቆ የሚኖር መሆኑን ከድርጅቱ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፤ በኢትዮጵያ ለሚገኙ አብዘሃኛዎቹ ተረጂዎች የእርዳታ እህል የሚቀርበው ከአሜሪካን መንግስት ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ እና ከአለም የምግብ ፕሮግራም መሆኑንም ተጠቁሟል።

አዲስ ስታንዳርድ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ባሰረጫው ዘገባ በኢትዮጵያ ከለጋሾች የተገኘ የምግብ እርዳታ ላልታለመለት አላማ እየዋለ የሚገኘው በተቀናጀ፣ በተደራጀ መንገድ መሁኑ እና ተግባሩ የፌደራል እና የክልል ተቋማትን ያሳተፈ በሰባት ክልሎች የተፈጸመ ነው መባሉን አስታውቋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.