ዜና፡ በኢትዮጵያ በእገታ ላይ የነበረው እስራኤላዊ በጸጥታ ሀይሎች ጥረት መለቀቁ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም፡- ከሶስት ሳምንታት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ ጎንደር አከባቢ በዜግነት እስራኤላዊ የሆነ አንድ ግለሰብ በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በጎንደር ታግቶብኛል ሲል የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል። እስራኤላዊው የታገተው ማስለቀቂያ ገንዘብ በፈለጉ ሀይሎች መሆኑም በዘገባው ተጠቁሟል።

ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም የወጡ የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን በዘገባቸው እንዳስታወቁት ደግሞ በእገታ ላይ የነበረው እስራኤላዊ በኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ጥረት መለቀቁን ዘግበዋል። የ79 አመቱ እስራኤላዊ ፍራንሲስ አደባባይ የኢትዮጵያ ልዩ ሀይሎች በሱዳን ድንበር አቅራቢያ ከአጋቾች ጋር ባካሄዱት ፍልሚያ ማስለቀቃቸውን ዘገባዎቹ አመላክተዋል።

ቤተ እስራኤላዊው ፍራንሲስ አደባባይ እገታ እንደተፈጸመበት በማስመሰል ከቤተሰቦቹ የሚገኝን ገንዘብ ለመውሰድ በማለም የፈጸመው የማጭበርበር ተግባር ነው ብሎ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ማመኑን የእስራኤል የዜና አገልግሎት ዘገባ ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል። በዚህም ሳቢያ ታጋቹን እስራኤላዊ ለማስለቀቅ የሚደረገው ጥረት በእስራኤል ባለስልጣናት እንዲቋረጥ መደረጉን በዘገባችን ጠቁመናል።  ቤተሰቦቹ በበኩላቸው በባለስልጣኑ ግኝት ላይ አለመስማማታቸውን እና ፍራንሲስ አደባባይ አሁንም በእገታ ላይ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው በዘገባችን ተካቷል።

የዛሬዎቹ ዘገባዎች እንደሚላመላክቱት ከሆን በእገታ ላይ የነበረው አደባባይ ከሁለት ልጆቹ ጋር በጎንደር መገናኘቱን ጠቁመው በቅርቡ ወደ እስራኤል እንደሚያመራ አስታውቀዋል። የእስራኤል ባለስልጣናት በተሳሳተ መረጃ አደባባይ ለገንዘብ ሲል እንደታገተ አስመስሏል የሚል እምነት አድሮባቸው አንደነበርም ገልጸዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.