ዜና፡ አንድ እስራኤላዊ በጎንደር መታገቱን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5/2015 ዓ.ም፡- በዜግነት እስራኤላዊ የሆነ አንድ ግለሰብ በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በጎንደር ታግቶብኛል ሲል የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቀ። እስራኤላዊው የታገተው ማስለቀቂያ ገንዘብ በፈለጉ ሀይሎች መሆኑም ተጠቁሟል።

ታጋቹን እስራኤላዊ ለማስለቀቅ ዲፕሎማቶች ከአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች እና ከኢንተርፖል ጋር በመቀናጀት እየሰሩ እንደሚገኙ መስሪያ ቤቱ ገልጿል። ታጋቹ እስራኤላዊ እድሜ በ70ዎቹ መሆኑን የጠቀሙት ዘገባዎች ወደ ጎንደር ያቀናው ከቀናት በፊት መሆኑን አስታውቀዋል።

ከአጋቾቹ ጋር ኢንተርፖል እና የአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች ግንኙነት ለማድረግ መሞከራቸውን እና በወቅቱም ማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቃቸውነ ዘገባዎቹ ጠቁመዋል። ለማስለቀቅ የተጠየቀው ገንዘብ በመጀመሪያ በሚሊዮኖች እንደነበረ አና ቆየት ብሎ በተደረገ ውይይት ወደ ሺዎች መውረዱን የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች አመላክተዋል። ታጋቹ እስራኤላዊ በድምጽ ለቤተሰቦቹ በላከው መልዕክት እርዱኝ፣ በጫካ መሃል ላይ እገኛለሁ ማለቱን ያስነበቡት ዘገባዎቹ ዝናብ እየዘነበብኝ ነው እርዱኝ፤ እሁድ ዕለት መምጣት ነበረብኝ ግን መቆየቴ አይቀርም ይመስላል፤ ልጆቼ እርዱኝ፣ አሁን ያለሁበት ሁኔታን ለጠላቶቼም አልመኘውም ሲሉ እንደሚደመጡ አስታውቀዋል።

የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ ዜጋው ጎንደር አቅራቢያ መታፈኑን ሰኞ እለት ሪፖርት እንደተደረገለት አስታውቆ አፋኞቹ ወንጀል ለመፈጸም ተነሳስተው ያደረጉት ነው ሲል ገልጿል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.