ዜና፡ በመተማ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በስደተኞች መጠለያ፣ የግል ንብረቶቻቸውና የህክምና ቁሳቁስ ላይ ጉዳት ማድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25/2015 ዓ.ም፡- ምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ባለፉት ጥቂት ቀናት የዘነበው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ከሱዳን ተፈናቅለው በስፍራው የሚገኙ የስደተኞች መጠለያና የግል ንብረቶቻቸው እንዲሁም የህክምና ቁሳቁስ ላይ ጉዳት በማድረስ የህክምና አገልግሎት ተቋርጦ እንዲቆይ አድርጓል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

በአካባቢው የዘነበው ዝናብ በመተማ ድንበር መግቢያ እና ማንደፍሮ ተራራ የሚገኙ ስደተኞች ላይ እና የእርዳታ ድርጅቶች ላይ ተፅዕኖ አድርሷል ሲል ድርጅቱ ትለንት ባወጣው መግለጫ ገልጧል፡፡ የክረምትን ዝናብ መቋቋም የሚችሉ በቂ መጠለያዎች ቀድመው ካልተዘጋጁ ጉዳቱ የከፋ እንደሚሆንና ይህም በአካባቢው ህብረተሰብ የማስተናገድ አቅም ላይ የበለጠ ጫና የሚፈጥር ይሆናል ብሏል።

በተለይ ግንቦት 20፣ 2015 ምሽት የጣለው ከባድ ዝናብ ከሱዳን በመጡና እየመጡ ላሉት ስደተኞች ቀድሞውን ላለው ፍላጎት ለሟሟላት እጠረት ላይ ተጨማሪ ፈተና ፈጥሯል ሲል ገልጧል፡፡ በመተማ ድንበር አካባቢ ያሉት ጊዚያዊ መጠለያዎችና የስደተኞቹ የግል ቁሳቁሶች ወድሟል ብሏል፡፡

የሱዳን ቀውስ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ወደ 48 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች አማራ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የገለፀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቤንሻንጉል ጉምዝ ጉባ ወረዳ የሚገኙ ከ11 ሺህ በላይ ተመላሾች ምግብ እና መጠለያን ጨምሮ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል ጠቅሶ አስቸኳይ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግም አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ አጠቃላይ ወደ 48 ሺህ ከሚጠጉ ስደተኞች ውስጥ ከ36 ሺህ በላይ የሚሆኑት ከሚያዚያ 13 አስከ ግንቦት 23 በመተማ በኩል መግባታቸውን ጠቅሶ በቀን ከ1000 በላይ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በሚያዚያ መገባደጃ እና ግንቦት ወር ላይ ከ 11,700 በላይ መደበኛ ያልሆነ ስደተኞች በቤንሻንጉል ጉምዝ መግባታቸውን የክልሉና የወረዳ አመራሮች ገልፀዋል ብሏል፡፡

ወቅቱ የዝናብ ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በድንበር መግቢያዎቹ አካባቢ የተጨናነቀ ሰፈራ በመኖሩ ወረርሽኝ የመከሰቱ አጋጣሚ አሳሳቢ ነው ያለው ሪፖርቱ በቀጣይ እየመጣ ያለው ክረምት የሚያስከትለውን አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል አደጋን መቋቋም የሚችሉ መጠለያዎች እና መሰረተ ልማቶች መዘርጋት፣ ስደተኞችን ከድብበር አካባቢ ወደ ሌላ ቦታ ማዘዋወር እንዲሁም የውሃ፣ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና መበቂያን ማጠናከር ያስፈልጋል ሲል ጠቁሟል።

በውስን አቅም የኢትዮጵያ መንግስት እና ሌሎች የሰብአዊ እርዳታ አጋሮች ትኩስ ምግብ፣ የጤና አገልግሎት፣ የተመጣጠነ ምግብ ምርመራ ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እና ስደተኞችን ወደ ሌላ ቦታ የመዛወር ስራዎችን በማቅረብ ድጋፍ እየሰጡ ነው ሲልም አክሎ ገልጧል።

በተጨማሪም የድርግቱ ሪፖርት ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ያሉት ስደተኞች አሁንም በመቀጠላቸው እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቁ አለመሆኑን ገልፆ በድንበር አካባቢ ያሉ አርዳት የሚያስፈልጋቸውን ሰዎችን ለመርዳትና የህይወት ለማትረፍ አስቸኳይ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል ሊል አስታውቋል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.