ዜና: የአለም ምግብ ፕሮግራም አማራ ክልል ዋግምራ ዞን እርዳታ መላኩን አስታወቀ



ምንጭ፡ የአለም ምግብ


ሐምሌ 20፣ 2014 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፦በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) መስሪያ ቤት በአሁኑ ሰዓት የእርዳት እህል የጫኑ ከባድ መኪናዎች አማራ ክልል ወደማገኙ  አበርገሌ፣ ፃግብጂ፣ እና ዝቋላ ወረዳዎች ከአንድ አመት በላይ ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በመግባት ላይ መሆናቸውን አስታወቀ

በአካባቢው የተከሰተው የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ከአደጋ ጊዜ በላይ ተደራሽ መሆን አለበት ያለው ድርጅቱ የህይወት አድን ምግብ የማጓጓዝ ሂደት ቀጣይነት መኖር አለበት ብሏል።

ሃምሌ 5፣ 20141 ዓ.ም  በአዲስ ስታንዳርድ  ባቀረበችው የዜና ትንታኔ በዋግ ኽምራ ተፈናቃዮች ላይ ያለውን የጤና ችግር መዘገቧ ይታወሳል። በተለይ በአበርገሌ ወረዳ የወባ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ ከፍተኛ የምግብ እጥረት እና አጣዳፊ ትውከት በሽታ በመከሰቱ ለስምንት ሰዎች ሞት ምክኒያት መሆኑን አዲስ ስታንዳርድ የዞኑን ጤና ጥበቃ ቢሮ በመጥቀስ ሪፖርት አድርጋለች።

የተባበሩት መንግስታት ሀዚሁ ሃምሌ ወር መጀመሪያ  ሳምንት ባወጣው ሪፖርት በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በቱርክ መንግስት በተገነባ የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ በያዝነው አመት ሰኔ 22 ቀን በተደረገው ሁለገብ ኤጀንሲ ግምገማ ተፈናቃዮች በተጨናነቀ ሁኔታ እንደሚገኙ እና ከደረጃ በታች ያሉ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዳገኘ አመልክቷል።

ጣቢያው ከሚያዝያ 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 3000 ተፈናቃዮችን እና ስደተኞችን በማስጠለል ላይ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ሲሰጥ የነበረው ዕርዳታም በቋሚነት ሲደረግ እንዳልነበረ  እና በቂም እንዳልሆነም ተጠቅሷል። ሪፖርቱ አክሎም “ተንቀሳቃሽ የጤና አገልግሎት የለም” ያለ ሲሆን  አንድ የገላ መታጠቢያ  ብሎክ ብቻ እንዳለ ጠቅሶ  የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት እንደሌለም ተናግሯል። በመጸዳጃ ቤት እጦት ምክንያት ሰዎች ክፍት በሆኑ ቦታዎች እየተጠቀሙ መሆኑን አንስቶ ሁኔታውን “የጤና ጠንቅ” ነው ብሎታል። በቂ መጠለያ ባለመኖሩ ተፈናቃዮች እና ስደተኞች ለጤና እና ለጥበቃ ስጋት ተጋልጠዋል ሲልም የተ.መ.ድ ሪፖርት አመልክቷል።

በዚህ ዝናባማ ወቅት ሰዎች በአብዛኛው በኮንክሪት ወይም በባዶ መሬት ላይ ከላስቲክ በተሰሩ መጠለያ ውስጥ እየኖሩ መሆኑን ተናግሮ ምግብ፣ የጤና አገልግሎቶች፣ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ ነገሮች እንደ ፍራሽ እና የግል ንፅህና መጠበቂያ እንዲሁም አልባሳት በቅድሚያ ለተፈናቃዮቹ አስፈላጊ መሆናቸውንም ተገልጿል። በዋግኽምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች 95,000 ተፈናቃዮች የኑሮ ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን እና 40,500 ተመላሽ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ መጠለያ ወይም በፈራረሱ ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ ከመጠለያው ጣቢያ  እና ከምግብ ነክ ካልሆኑ አጋር ድርጅቶች  ገለጻ ለመረዳት ተችሏል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.