አዲስ አበባ የካቲት 28 2014 ፣ባለፈው ታህሳስ ወር በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ለአሶሼትድ ፕሬስ ይሰሩ የነበሩትን ጋዜጠኛ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያው ቶማስ እንግዳ ላይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለመርማሪ ፖሊስ ዛሬ በዋለው ችሎት 14 ተጨማሪ ቀናትን ሰጠ።
አርብ ጥር 4 በዋለው ችሎት ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናቀቅ 14 ቀናት ጠይቆ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለዛሬ ችሎት እንዲያቀርብ ማዘዙ ይታወሳል። መርማሪ ፖሊስ በዛሬው እለት መዝገቡን ለፍርድ ቤት አቅርቦ ተጨማሪ 14 ቀናት ጋዜጠኞች በእስር እንዲቆዩ እና ምርመራውን እንዲቀጥል ጥያቄ አቅርቧል።
ፖሊስ ከዚህ ቀደም በዋለው ችሎት ከጋዜጠኞች የተወሰዱ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ለምርመራ ወደ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ የመላክ ስራ መጠናቀቁን እና ከኤጀንሲው በጋዜጠኞቹ ላይ ተጨማሪ “የቴክኒክ ማስረጃዎችን” እንዲልክ እየጠበቀ መሆኑን ተናግሮ ነበር።
ፖሊስ ጋዜጠኞቹን ከ”አሸባሪ ድርጅቶች” ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ተጠርጣሪዎች እየመረመረ መሆኑን ገልጿል።ባለፈው አመት ታህሣሥ አጋማሽ ላይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሁለት ጋዜጠኞችን እና አንድ የካሜራ ባላሙያን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን (ኦነግ) በአለም አቀፍ ደረጃ አስተዋውቀዋል በማለት ማሰሩን አስታውቋል። ”በምዕራብ ሸዋ ዞን ሸኔ(የመንግስት ባለስልጣናት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለማመልከት የሚጠቀሙበት ቃል) ለማስተዋወቅ ብዙ ገንዘብ የተከፈላቸው ጋዜጠኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ናቸው” ሲል መግለጫው ዘግቧል። በእስር ላይ በነበረበት ወቅት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሲሰራ የነበረው አዲሱ ሙሉነህ ከእስር ተፈቷል።
ፍርድ ቤቱ በጋዜጠኛ አሚር አማን እና በካሜራ ባለሙያው ቶማስ እንግዳ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ለመጋቢት 9፣ 2014 ቀን እንዲሆን ትእዘዝ ሰቷል። አስ