አዲስ አበባ፤ መስከረም 06/2015 ዓ.ም፦ የወልድያ ከተማ አስተዳደር ሰላም እና የሕዝብ ደኅንነት ጽሕፈት ቤት ሕወሃት ያሰማራቸው “ሰርጎ ገቦች” ና “ጸጉረ ልውጥ” ሲል የከሰሳቸውን ከ1 መቶ 23 በላይ ተጠርጣሪዎች ይዞ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ጽሕፈት ቤት ኅላፊ አቶ ጌታቸው ካሳው ለአሚኮ አስታወቁ ።
“የሕወሃት ዓላማ በሰላማዊ ከተሞች ሰርጎ ገቦችን አሰማርቶ ሽብር መፍጠር እና መዝረፍ” ነው ያሉት ኅላፊው ወጣቱ እና ሕዝቡ ይህንን ቀድመው በመረዳታቸው ተናበው ለከተማዋ ሰላም በጋራ እየሠሩ ነው ብለዋል።
የወልድያ ከተማ አስተዳደር መግለጫ አክሎ እንደከሰሰው “ሕወሃት እንደ አንድ የትግል ስልት ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ ሰርጎ ገቦችን በማሰማራት የሃሰት መረጃን እያሰራጨ ሰላማዊ እንቅስቃሴን እንደሚያውክ” እና ባለፉት ወራትም “በተለያዩ አካባቢዎች ሕወሃት ሰርጎ ገቦችን በመጠቀም ለዘረፋ እና ሕገ ወጥ ድርጊቶች ሲጠቀምበት ቆይቷል” ብሏል።
“ተደጋጋሚ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እና የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸም ጥረት ከሚደረግባቸው አካባቢዎች አንዷ ደግሞ የወልድያ ከተማ ናት” ሲል መግለጫው አስታውቆ በከተማዋ ሕዝባዊ ሠራዊት በማደራጀት እና ማሕበረሰቡን በማንቃት በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሰራታቸው ውጤት እንዳመጣ የቀድሞ ሠራዊት አባሉ እና የወልድያ ከተማ ነዋሪው መቶ አለቃ አልታሰብ ወደጀ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
አቶ ጌታቸው “የከተማ አስተዳደሩ ሕዝባዊ ሠራዊት፣ ፖሊስ እና ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች በጥምረት ለ24 ስዓታት ከተማዋን በመጠበቃቸው በርካታ ውጤቶች ተገኝተዋል” ያሉ ሲሆን አክለውም “የሰዓት እላፊን በማክበር፣ የተለየ ክስተት ሲስተዋል በመጠቆም እና ሕዝቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቁ ማሕበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴዎች እንዳይስተጓጎሉ” ተደርጓል ብለዋል።
ሃላፊውም አክለው “የሕልውና ስጋቱ” በአስተማማኝ ደረጃ እስኪቀለበስ ድረስ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። አስ