ዜና፡ ዛምቢያ 44 ያለፈቃድ ይኖሩ የነበር ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከሀገሯ አስወጣች; አንድ ስደተኛ በአውሮፕላን ማረፊያው ህይወቱ አለፈ

በ2009 ዛምቢያ ከ15 እስከ 38 ዓመት የሆናቸው 150 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ፕሬዝዳንታዊ ይቅርታ ከእስር ቤት ፈትታ ነበር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5/2015 ዓ.ም፡- የዛምቢያ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት 44 ያለፈቃድ ይኖሩ የነበር ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ቃል አቀባዩ ለዛምቢያ ሚዲያ ተናግረዋል። ሰኞ እለት ስደተኞቹ በኬኔት ካውንዳ አለም አቀፍ አውሮፕላን ለመሳፈር በዝግጅት ላይ እያሉ ከስደተኞቹ መካከል አንዱ መሞቱን የኢሚግሬሽን ዲፓርትመንት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት ናማቲ ሺንካ ተናግረዋል፡፡ በዜና ዘገባዎቹ ውስጥ የሟቹ ስም አልተገለጸም፡፡

የዛምቢያ መገናኛ ብዙሀን ቃል አቀባዩን ጠቅሰው እንዳዘገቡት የ20 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ ህይወቱ ማለፉ በአውሮፕላን ማረፊያው በሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ተረጋግጧል። “የግለሰቡ የሞቱ መንስኤ ገና አልታወቀም። የተቀሩት 43ቱ በሰላም ከአገሪቱ ተሸኝተዋል” ሲል ናማቲ ተናግረዋል።

እንደ እሳቸው ገለጻ ከጳጉሙ3 እስከ መስከረም 2 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ከዛምቢያ ወደ ኢትዮጵያውያ የተመለሱ ስደተኞች ቁጥር 107 አድርሶታል።

ናማቲ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በመታገዝ ከአፍሪካ ቀንድ ከሚገኙ ሀገራት የመጡ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች የተሻለ ኑሮ ፍለጋ አደገኛ ጉዞ ማድረግ መቀጠላቸው አንዳሳሰባቸው ገፀዋል።

ባሳለፍነው አመት ሰኔ ወር ላይ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ድጋፍ ጋር ባደረጉት የማረጋገጫ ልምምድ መሰረት በማላዊ የነበሩ ከ500 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው የመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው የጉዞ ሰነድ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተሰጥቷቸዋል።

የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደገለፀው ማላዊ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚወስደው የየብስ መስመር ላይ የምትገኝ የመተላለፊያ ሀገር ነች፣ ብዙ ጊዜ ‘ደቡባዊ መስመር’ በመባል ትታወቃለች። መንገዱን በዋናነት ከኢትዮጵያ እና ከሶማሊያ የመጡ መደበኛ ባልሆኑ ስደተኞች እስከ ኬፕታውን ድረስ ያለውን የስራ እድል ፍለጋ ለማግነት ይጠቀሙበታል። በመሆኑም ደቡብ አፍሪካ ከመግባታቸው በፊት በታንዛኒያ፣ ማላዊ፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ ወይም ሞዛምቢክ ማለፍ አለባቸው።

ስደተኞቹ በሚያቋርጡት ሀገራትም ሆነ በመድረሻ ቦታ ለጥቃት፣ ብዝበዛ እና እንግልት ይጋለጣሉ ሲል የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ተናግሯል።

በ 2008 የዛምቢያ ፖሊስ በሴሬንጄ 100 መደበኛያልሆኑ ኢትዮጵያውያንስደተኞችን ጭኖ ከደረቅ ሀይቅ ሰርዲን ከረጢት ጀርባ ካፔንታ እየተባለ በሚጠራው የጭነት መኪና ተይዟል። በማዕከላዊ ግዛት በታላቁ ሰሜን መንገድ በካኖና የፖሊስ ፍተሻ ጣቢያ የተያዘው የጭነት መኪና ከናኮንዴ ተነስቶ ዛምቢያ ውስጥ ወዳልታወቀ ቦታ ነበር። ተሽከርካሪው ከናኮንዴ ወደ ዛምቢያ ውስጥ ወዳልታወቀ ቦታ ሲጓዝ በማዕከላዊ ግዛት በታላቁ ሰሜናዊ መንገድ በሚገኘው የካኖና ፖሊስ ፍተሻ ላይ ተይዞ ነበር።

በ2010 ዛምቢያ ከ15 እስከ 38 እድሜ መካከል የሚገኙ 150 ኢትዮጵያውያንስደተኞችን የፕሬዝዳንት ይቅርታ ካገኙ በኋላም በእስር ላይ የነበሩትን ስደተኞች ፈትታ ነበር። ስደተኞቹ በዛምቢያ ከአንድ እስከ አምስት ዓመት ድረስ ታስረው የነበሩ ሲሆን በተለያዩ የሀገሪቱ እስር ቤቶች የተለያዩ ከስደት ጋር የተያያዘ ቅጣቶችን ሲቀጡ እነደነበር የዛምቢያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.