አዲስ አበባ ፣መጋቢት 30፣ 2014 – የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማኅበር ኮንፌዴሬሽን በትናንትናው እለት ባካሄደው የግማሽ አመት ኮንፈረንስ ላይ መንግስት ለኢንዱስትሪ ፖርክ ሰራተኞችን የስራ ዋስትና በተመለከ መፍትሄ እንዲሰጥ ተጠየቀ። ኮንፌድሬሽኑ ጨምሮም በኑሮ ውድነቱ ላይ ዘላቂ እና ተጨባጭ የሆነ መፍትሄ በተለይም ዝቅተኛ ክፍያ ተከፋይ ለሆኑና ለኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞች እንዲሰጥ መንግስትን አሳስቧል።
የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ካሳሁን ፎሎ እንዳሉት አሁን ላይ ያለው የኑሮ ውድነት ሰራተኛውን በጣም እየጎዳው ይገኛል። ” ሰራተኞች በተለይም ዝቅተኛ ተከፋዩች ቤተሰብ ማስተደዳደር ቀርቶ ለራሳቸው የሚበሉት አጥተዋል። የሚያገኟትን ትንሽ ገንዘብ የቤት ኪራይ ይከፍላሉ።” ፕሬዝዳንቱ ጨምረው በኢትዮጵያ የተከሰተዉ የኑሮ ውድነት የጀመረው ከኮቪድ ወረርሺኝ በፊት መሆኑን አስታውሰዉ፣ የኮቪድ ወረርሽን ያመጣው የኢኮኖሚ መዋዠቅ በትግራይ ክልል የነበረው ጦርነት እና አለማቀፉ የዩክሬይን እና ሩሲያ ጦርነት ችግሩን የከፋ አድርጎታል ብለዋል።
ፕሬዘደንቱ አክለው ፣ “በኮቪድ ወረርሽኝ ወረርሽኝ ወቅት መንግሥት አዳዲስ መመሪያዎችን አውጥቶ ለባለሀብቶች የዕዳ ስረዛን ተግባራዊ አድርጓል። ይህም በከፊል እንደ ሆቴሎች አገልግሎት መስጠት ማቆም በስተቀር የሰራተኞችን መቀነስ እና ከስራ ከማሰናበት ታድጓል።” ሲሉ ተናግረዋል ።
ፕሬዝዳንቱ በተለይ በትግራይ የተካሄደውን ጦርነት በኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞች ላይ ሁለት ትልልቅ ጫናዎችን ማሳደሩን ጠቅሰዋል። “የመጀመሪያው በኮምቦልቻ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በጦርነቱ ወቅት የደረሰው ውድመት ሲሆን ሌላኛው በትግራይ ያለውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ጉዳይ በተመለከተ አሜሪካ፣ ለአፍሪካ ሀገራት ትሰጥ የነበረውን ከቀረጥ ነፃ ዕድል (አጎዋ) ለኢትዮጽያ መሰረዟ ነው።”
እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ በችግሩ ምክንያት ከስራቸዉ የተቀነሱ ሰራተኞች የኢኮኖሚ ቀውስ ፈጥሮባቸዋል ፤ ይህም እየተፈጠረ ያለው እና በቀጣይም የሚፈጠር ስለሆነ ችግሩ እንደነበረ ይቀጥላል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማኅበር ኮንፌዴሬሽን የአጎአን ጉዳይ በራሳቸው ለመፍታት ሞክረው የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ጋር ደርሰው የነበር ቢሆንም ነገርግን እዚህ መድረስ ከቻላችሁ ሂዱ እና የኢትዮጵያ መንግስት ለትግራይ ክልል የሚቀርበውን ሰብአዊ አቅርቦት እንዲያመቻችላቸው አሳምኑቸው በዚህም አግባብ ችግሩ ሊፈታ ይችላል ብለው እንደመለሷቸው ይናገራሉ።
ፕሬዝዳንቱ በጉዳዩ ዙሪያ በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመካሄድ ላይ ያሉ ውይይቶች እንዳሉም ጠቁመዋል።አስ