ዜና: የአማራ ክልል ምክር ቤት ደብረታቦርና ወልድያ ከተሞች ወደ ሬጂዮፖሊታንት ደረጃ እንዲያድጉ ወሰነ

የወልድያ ከተማ ። ምስል የወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 – የአማራ ክልል መሥተዳደር ምክር ቤት 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ሰኔ 25/2014 ዓ.ም በተካሄደበት ወቅት የደብረታቦርና ወልድያ ከተሞች ወደ ሬጂዮፖሊታንት ደረጃ እንዲያድጉ ወስኗል በማለት የክልሉ ሚዲያ አሚኮ ዘግቧል።

“ሬጂዮፖሊስ” (regiopolis) ከከተማ ወይም ከሜትሮፖሊታን አካባቢ ወይም እምብርት ውጭ ያለ ከተማ ሲሆን በአንድ ክልል ውስጥ ለልማት ራሱን የቻለ አንቀሳቃሽ ኃይል ሆኖ የሚያገለግል ነው።

ምክር ቤቱ ውሳኔውን ለማስተላለፍ የቻለው ከተሞቹ ሪጆፖሊታንት ደረጃ ለማደግ የተቀመጡ መስፈርቶችን ስለማሟላታቸው በጥናት ተደግፎ የቀረበለትን ሰነድ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ መኾኑን ከክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት የተገኘን መረጃ አሚኮ በመጥቀስ ዘግቧል።

ምክር ቤቱ ባለፈው ዓመት ደብረብርሃን፣ ደብረ ማርቆስና ኮምቦልቻ ከተሞች ወደ ሪጆፖሊታንት ደረጃ እንዲያድጉ መወሰኑ ይታወሳል።

በአማራ ክልል በተለያዬ ደረጃ የሚጠሩ 660 ከተሞች እንዳሉና ከክልሉ ሕዝብ 22 በመቶ የሚኾነው የከተማ ነዋሪ እንደኾነ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ያመላክታሉ። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.