ዜና: በኢትዮጵያ ጦርነት “የጦር ወንጀልና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች” ስለመኖራቸው አሳማኝ ምክንያቶች አሉ፣ ትግራይ “ስልታዊ በሆነ መንገድ” የቁሳቁስና ለህልውና አስፈላጊ አገልግሎቶች ተነፍጋለች: የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መርማሪዎች

በኤርትራ ወራሪ ሃይሎች ከተጎዱት ሆስፒታሎች መካከል አንዱ የትግራይ ሽሬ ሆስፒታል ነው።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10/ 2015 ዓ.ም፡- የአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች በኢትዮጵያ (ICHREE) ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት “ከህግ አግባብ ውጭ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ጾታዊ ጥቃት እና በሲቪል ህዝብ ላይ የደርሰው ረሃብ እና የመሳሰሉ ጥሰቶች እ.አ.አ ከህዳር 3 ቀን 2020 ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈፀመ መቆየቱ ለማመን የሚረዱ ምክንያቶች አሉ” ብሏል። አክሎም “በብዙ አጋጣሚዎች እነዚህ ጥሰቶች የጦር ወንጀሎች እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ናቸው ብሎ ለማመን ተመጣጣኝ ምክንያቶች ነበሩ” ብሏል።

ኮሚሽኑ በተጨማሪም “የፌዴራል መንግስት እና አጋር የክልል መንግስታት የትግራይን ህዝብ ስልታዊ በሆነ መንገድ እንደ ጤና መጠበቂያ ፣መጠለያ ፣ ንፅህ ውሃ፣ ትምህርት ምግብ እና ለህልውና አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን እና አገልግሎቶችን ለማሳጣት የተነደፉ ሰፊ እርምጃዎች መተግበራቸውን ለማሳመን የሚያስችል በቂ ምክንያት አግኝቻለሁ ብሏል።

በቅርቡ የወጣው የ UNOCHA ዘገባ እንደሚያመለክተው “ከሰመራ – መቀሌ መስመር ላይ የሰብአዊ እርዳታዎችን የሚመላልሱ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ከነሐሴ 18 ቀን ጀምሮ በመቋረጡ የሰብአዊ አቅርቦቶችን ተቋርጠዋል። በአዲስ አበባ እና መቀሌ መካከል በሳምንት ሁለት ጊዜ ይበር የነበረው እና በቅርቡ የሶስተኛ ሳምንት በረራ ማዘጋጀቱን ይፋ ያደረገው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ አየር አገልግሎት (UNHAS) በረራዎችም ከነሐሴ 26 ቀን ጀምሮ በመቋረጡ የሰብአዊ ሰራተኞችን እንቅስቃሴ እና ለሰብአዊ ተግባራት የሚውል የገንዘብ ዝውውር ላይ እንቅፋት ፈጥሯል።

የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ “በትግራይ ያለው የሰብአዊ ሁኔታ መጠን እና የሚቆይበት ጊዜ አስደንጋጭ ነው” ብለዋል። “የመሠረታዊ አገልግሎቶችን፣ የምግብ፣ የጤና አጠባበቅ እና የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትን በስፋት እንዳይደርስ መከልከል በሕዝቡ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ በመሆኑ በሰው ልጆች ላይ የተፈፀመ ወንጀል መሆኑን የምናምንበት በቂ ምክንያት አለን ፡፡ የፌደራል መንግስት ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀመ ነው ብለን የሚሳምን ምክንያት አለን” ብለዋል።

ኮሚሽኑ በስራው ወቅት “የጊዜ እና የሰው ሃይል ችግር፣ የቦታ እና የሰነድ አቅርቦት እጥረት” ያጋጠመው ሲሆን ከእነዚህም መካከል በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካላት ሰነዶችን እና የአስፈላጊ ቁሳቁሶችን እንዲያካፍሉት ላቀረበው ጥያቄዎችም ከቆይታ በኋላ መልስ ማግኘታቸውንና በአብዛኛዎቹ የተዛቡ መሆናቸውንና ገልጧል። በዚህም የተነሳ በሪፖርቱ ውስጥ ሁሉንም ክስተቶች ወይም አጠቃላይ የሽግግር ፍትህ ስትራቴጂን ማቅረብ አይችልም ብሏል፡፡

በተጨማሪም ባለ 19 ገፅ ዘገባው በትግራይ እና በአማራ ክልል ግጭቶች” ብቻ ላይ የተወሰነ እና በየተመረጡ ክስተቶች ላይ የተመሰረተ ነው። ይሁን እንጂ በሰዎች ላይ በተለይም በኤርትራ ስደተኞች ላይ የሚፈጸሙ አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በስፋት ይፋ አድርጓል። በኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት፣ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ጦር ሚሊሻ እና መደበኛ ያልሆኑ የፋኖ ታጣቂ ቡድን እና የትግራይ ሃይሎች በተለያየ ደረጃ የመብት ጥሰት ፈፅመዋል።

በትግራይ ውስጥ የቀጠለው ወታደራዊ ጦርነት እንደገና መጀመሩ ኢትዮጵያን ወደ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን የኮሚሽኑ ማስጠንቀቁ የበለጠ አሳሳቢ እንዲሆን አድርጓል።

ካቀረባቸው አስቸኳይ ምክረ ሐሳቦች መካከል ኢጋድ፣ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የፀጥታው ምክር ቤት፣ እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሁኔታ በአጀንዳዎቻቸው ላይ በማስቀመጥ ሰላም፣ መረጋጋትን ወደ ነበረበት ለመመለስ ያለመ እርምጃ መውሰድ፣ እና በአካባቢው ያለው ፀጥታ፣ ተጨማሪ ጥሰቶችን እና በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግጋት እና በሰብአዊ ህግጋት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን እንዲያቆሙ አስገንዝቧል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.