አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም፡- በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ሐምሌ 20 እና 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሄደው የሩሲያ አፍሪካ ስብሰባ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩ የፑቲን የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ አማካሪ መናገራቸውን የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሴንት ፒተርስበርግ ይፋዊ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ እና ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ተገናኝው እንደሚመክሩ የጠቆሙት የክሬሚሊን ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ ሁለቱም መሪዎች በጋራ ቁርስ እንደሚመገቡ ገልጸዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ከጠ/ሚኒስትር አብይ በተጨማሪ ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩ ያስታወቁት ዩሪ ኡሻኮቭ ሁለቱም መሪዎች ለጋዜጠኞች በጋራ መግለጫ እንደሚሰጡ አመላክተዋል። የጋራ ምሳም ይኖራቸዋል ብለዋል።
የጀመሪያው የሩሲያ-አፍሪካ ስብሰባ የሩሲያዋ ሶቺ ከተማ በ2019 ላይ ማስተናገዷ የሚታወስ ነው፤ በወቅቱ ሁለተኛው የሩሲያ አፍሪካ ስብሰባ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጾ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጣሊያን ሮም በተካሄዱ በተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ስብሰባና የዓለም አቀፍ የልማትና ፍልሰት ጉባዔ ላይ መሳተፋቸውን ጠ/ሚኒስትሩ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሮም ቆይታ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ልምድና ተሞክሮዋን ያጋራችበትና ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ ያከናወነችበት ነው ሲሉ የጠ/ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም መናገራቸውን በመንግስ መገናኛ ብዙሃን የተላለፉ ዘገባዎች አመላክተዋል።
በሌላ ዜና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎደሚር ዜለንስኪ ከጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ማውራታቸውን እና አብይ አህመድ ዩክሬንን እንዲጎበኙ መጋበዛቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ኢትዮጵያ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረሰችውን ወረራ ለማውገዝ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔ ላይ ድምጽ ከመስጠት ከተቆጠቡ ስምንት ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት አንዷ መሆኗ ይታወቃል፡፡
በዩክሬን ፕሬዝዳንት ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ ላይ እንደዘገበው፣ ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት የስልክ ንግግር፣ ሩሲያ የዩክሬን የእህል ምርት በጥቁር ባሕር በኩል ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ ከዩክሬን ጋር የነበራት ስምምነት ስለማብቃቷ፣ ህገ-ወጥ የባህር ላይ ትራፊክ እገዳ እና በዩክሬን ወደብ እና የኢነርጂ መሠረተ ልማት ላይ ስለደረሰው ጥቃቶች ተወያይተዋል፡፡ አስ