ዜና፡ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎደሚር ዜለንስኪ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ዩክሬንን እንዲጎበኙ ጋበዙ

አዲስ አበባ፣ ሓምሌ 14 /2015 ዓ.ም፡- የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎደሚር ዜለንስኪ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ዩክሬንን እንዲጎበኙ ጋበዙ፡፡ ቮሎደሚር ዜለንስኪ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን የጋበዙት ሁለቱ መሪዎች ከሁለት ቀን በፊት ባደረዱት የስልክ ንግግር ነው፡፡

ኢትዮጵያ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረሰችውን ወረራ ለማውገዝ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔ ላይ ድምጽ ከመስጠት ከተቆጠቡ ስምንት ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት አንዷ ናት፡፡

በዩክሬን ፕሬዝዳንት ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ ላይ እንደዘገበው፣ ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት የስልክ ንግግር፣ ሩሲያ የዩክሬን የእህል ምርት በጥቁር ባሕር በኩል ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ ከዩክሬን ጋር የነበራት ስምምነት ስለማብቃቷ፣ ህገ-ወጥ የባህር ላይ ትራፊክ እገዳ እና በዩክሬን ወደብ እና የኢነርጂ መሠረተ ልማት ላይ ስለደረሰው ጥቃቶች ተወያይተዋል፡፡

በጠቅላይ ሚንስትር አብይ እና በቮሎደሚር ዜለንስኪ መካከል የተደረገው ይህ የስልክ ንግግር የመጀመሪያው ነው፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው፣ በሁለቱ አገራትና በአለም አቀፍ ጉዳይ ላይ አንዲሁም በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ሰላም ለማውረድ በሚረዱ ነጥቦች ላይ መምከራቸውን ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ዜለንስኪ አገራቸው ዩክሬን ወደ 300ሺህ ቶን የሚጠጋ ምግብ እንዲሁም ከዩክሬን የሰብአዊ ኢኒሼቲቭ የተገኘ ተጨማሪ 90 ሺህ ቶን እህል በጥቁር ባሕር እህል ኢንሺኤቲቭ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ማድረሷን ገልፀዋል፡፡ ዩክሬን ለአለም አቀፍ የምግብ ዋስትና መሆኗን  ያረጋገጡት ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን፣ በተለይም የፀጥታ እና ዲጂታላይዜሽን ጉዳዮችን ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.