ዜና፡ ይርጋጨፌ ቡና በቻይና ከሻይ ጋር በመቀላቀል ልዩ ጣዕም ፈጥሯል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22/2015 ዓ.ም፡- ይርጋጨፌ ቡና በቻይና ከሻይ ጋር በመቀላቀል የፈጠረው ጣዕም በቻይናውያን ዘንድ ተወዳጅነት ማግኘቱን ዢንዋ ባስነበበው ዘገባ አስታውቋል። የቻይና ህዝብ ሻይ በመጠጣት ባህሉ የሚታወቅ ቢሆንም ቡናም በማጣጣም ላይ እንደሚገኝ ያስታወቀው ዘገባው አዲሱ የቻይና ትውልድ የቡና ፍላጎቱ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት 2022 በቻይና ገበያ በኦንላይን የተሸጠ የቡና መጠን 27 ነጥብ 6ቢሊየን ዶላር ማውጣቱን ያስታወቀው የዜና አውታሩ ከሶስት አመታት በኋላ ከ50 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚደርስ መተንበዩን አመላክቷል። ይህም በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የመጣውን የቻይናውያን የቡና ፍላጎት ያሳያል ተብሏል።

በቻይና በጥቂት ሰዎች ብቻ ይዘወተር የነበረው ቡና በአሁኑ ወቅት ሰዎች በቡድን ተሰባስበው የሚጠጡት ሁኗል ሲል ካሽ ኮፊ የተሰኘ የቡና ምርት በማቅረብ ላይ የሚገኝ የቻይና ኩባንያ መስራች ያኦ ሲዪ ገልጸውልኛል ሲል ያስነበበው ዢንዋ አዲሱ የቻይና ትውልድ የቡና ማሽኖችን በመግዛት እቤታቸው እንዴት ማፍላት እንደሚችሉ ትምህርት በመከታተል ላይ እንደሚገኙም ነግረውኛል ብሏል።

በቻይና የቡና ፍላጎት እንዲጨምር ካስቻሉ ምክንያቶች መካከል የሀገሪቱ መንግስት ለአፍሪካ የቡና አምራቾች ምርቶቻቸውን ወደ ቻይና ገበያ እንዲያቀርቡ ለማስቻል በሚል የአፍሪካ የግብርና ውጤቶች የገቢ ንግድ መመሪያዎች ቀላል እንዲሆኑ በማድረጉ ነው ሲል ዘገባው ጠቁሟል። የኢትዮጵያ ቡናን ጨምሮ በበርካታ የቻይና ገበያዎች ከአፍሪካ የተመረተ የሚል የግብርና ውጤት በስፋት እንደሚታይ የዜና አውታሩ ዘገባ አካቷል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.