አዲስ አበባ፣ህዳር8/2015 ዓ.ም፡-ኖርድ ቪንድ የተሰኘ መርከብ ከየክሬን የተገኘ እህል በመጫን በ”እህል ኮሪደር” ወደ ኢትዮጵያ የተንቀሳቀሰ መሆኑን የዩክሬን የመሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፕሬስ አገልግሎት በፌስቡክ ገፁ ላይ ማስፈሩን ጠቅሶ ዩክሬንኢንፎ ዘግቧል፡፡
“ኖርድ ቪንድ መርከብ በ‹እህል ኮሪደር› በኩል 27,000 ቶን ስንዴ ይዛ ከዩክሬን ወደ ኢትዮጵያ እየተጓዘች ነው” ሲል ዩክሬን ኢንፎ የፌስቡክ ፖስቱን ዋቢ አድርጎ ገልጧል፡፡
የዩክሬን ካቢኔ ሚኒስቴር በመስከረም ወር ዩክሬን ለኢትዮጵያ እና ሶማሊያ 14 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጭ የሚጠይቅ ስንዴ እንደምትልክ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ይህንንም የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በ77ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ያረጋገጡ ሲሆን፣ በጦርነቱ ምክኒያት ችግሮች ቢያጋጥሙንም ዩክሬን ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ለመስጠት መወሰኗን እና ተጨማሪ ስንዴም እንደምትልክ ገልፀው ነበር፡፡
በጀርመን መንግስት እና በተበበሩት መንግስታት ድርጅት የአለም የምግብ ፕሮግራም ድጋፍ፤ የመጀመሪያው የዩክሬን ስንዴ የተጓጓዘው ከኦዴሳ ወደብ ነበር፡፡
በአፍሪካ ቀንድ በድርቅ ክፉኛ ለተጎዱት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከዩክሬን የተበረከተ 50,000 ቶን ስንዴን በማጓጓዝ እና በማከፋፈል ጅርመንና ፈረንሳይ ድጋፍ ሰጥተው ነበር፡፡
ሁለቱ ሀገራት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለም የምግብ ፕሮግራም በኩል ለእያንዳንዳቸው 14 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር፡፡ “ጀርመን ወደ ኢትዮጵያ ለማድረስ የሚያስፈልገውን ወጭ የምትሸፍን ሲሆን ፈረንሳይ ደግሞ ወደ ሶማሊያ ለማድረስ የሚያስፈልገውን ወጭ ትሸፍናለች” ሲል መግለጫው አሳውቆ ነበር፡፡
እንደ የቅርብ ጊዜ ሪፖርት ከሆነ “መርከቧ በአፍሪካ፣ በኤስያ እና በአውሮፓ ውስጥ 269,000 ቶን የዩክሬን የግብርና ምርቶን የሚያጓጉዙት ስምንት መርከቦች አካል በመሆን በእህል ኮሪደር በኩል ተንቀሳቅሳለች”፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር የሆነው ቦዝቡሩን ኤም 40,000 ቶን የዩክሬን ስንዴ ለኢትዮጵያ እያጓጓዘ ነው፡፡
የዩክረዴን እህል ማጓጓዝ ከአለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመሆን የሚተገበር የሰብዓዊ ፕሮግራም ሲሆን የተጀመረውም እ.አ.አ ህዳር 05 ነው፡፡አስ