ትንታኔ፡የተሻለአገልግሎት የማግኘት ተስፋ እና ጉጉት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ደንበኞች ቁጥር አንድ ሚሊዮን አድርሶታል

ፒተር ንዴግዋ፣ የሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ በመስከረም 26 ቀን 2015 የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መደበኛ የመክፈቻ ምርቃት ስነስርዓት ላይ ንግግር ሲያቀርቡ። ፎቶ፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ

በአሰፋ ሞላ

አዲስአበባ፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ 10 ከተሞች የሙከራ አገልግሎት ካደረገ ብኋላ መስከረም 27፣ 2015 ዓ.ም ኔትወርክ እና አገልግለቱን በአዲስ አባባ በይፋ ከጀመረ የደንበኞቹ ቁጥር ወደ አንዲ ሚሊዮን መጠጋቱን ገልጿል።

የቴልኮ ተቋሙ ባለፈዉ ሳምንት ለሪፖርተር እንደገለፀው የደምበኞቹ ቁጥር 933,000 የደረሰ ሲሆን ይህ ቁጥር በዙህ ሳምንት አንድ ሚሊዮን ሊያልፍ እንደሚችል ግምት መኖሩን ጠቁሟል።

ኩባንያው በሀገሪቱ በሚገኙ 17 ከተሞች አገልግሎቱን በማስፋት እየሰራ ሲሆን እንደ ኬንያዉ ስታር ዘገባ ከሆነ አገልግሎት በጀመረበት የመጀመሪያው ወር 98.3 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ (806,000 ዶላር) ገቢ አግኝቷል፡፡

ኩባንያው ከጠቅላላ ገቢው ውስጥ 9.1 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ (74,000 ዶላር) ከአገልግሎት ያገኘ ሲሆን ቀሪው ከሞባይል ቀፎ ሽያጭ የተገኘ ነው ብሏል፡፡

በሀገሪቱ የመጀመሪያው የግል ቴሌኮም ኩባንያ የሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ የ4G ኢንተርኔት፣የድምፅ እና የመልዕክት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በባለ ‹07› ኮድ ኔትዎርኩ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም መስመር እንዲሁም አለም አቀፍ መስመሮሽ ጥሪዎች ማድረግ ያስችላል። በተጨማሪም የሞባይል ስልክ ሽያጭ አገልግሎቱን አቅርቧል፡፡

ኢትዮጵያውያን ከቴሌ ኮሙዩኒኬሽን ጋር የተዋወቁት በፈረንጆቹ 1894 ሲሆን፣ ያሁኑ ኢትዮ ቴሌኮም በጊዜው የተቋቋመውን ‹የቴሌፎን እና የቴሌግራፍ ማዕከላዊ አስተዳደር› መነሻ በማድረግ እያደገ የመጣ ተቋም ነዉ።

ኢትዮ ቴሌኮም ከመቶ ዓመት በላይ በሀገሪቱ ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ሲሆን በዋጋ ውድነት፣ በአገልግሎት መቆራረጥ እና በአዝጋሚ የኢንተርኔት አገልግሎቱ ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ይቀርቡበትነበርል፡፡ እንደ የአለም ባንክ ሪፖርት እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ የኢንተርኔት ፔኔትሬሽን ሬት ከ1 በመቶ በታች ሆኖ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም የተሻለ አገልግሎት የማግኘት ተስፋ እና አዲስ ነገር የመሞከር ዝንባሌ ሰዎች በገፍ ከወራት በፊት አገልግሎት ወደ ጀመረዉ ሳፋሪኮም እንዲሄዱ እያደረገ ነዉ።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አኑዋር ሶሳ ለሪፖርተር ሲናገሩ “ሰዎች በጣም ጓጉተዋል በየቀኑ ወደ 20,000 አዳዲስ ሰዎች ወደ ኔትዎርካችን ይመጣሉ” ብሏል።

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች ሳፋሪኮም በ ‹07› ኮድ አገልግሎት እንደሚጀምር ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በጉጉት እየጠበቁ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የሳፋሪኮም የሞባይል አገልግሎት ደንበኛ የሆኑት አዲስ ደርበው ‹ሳፋሪኮምን የመረጥኩት በፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎቱ እና አለም አቀፍ ኩባንያ እንደመሆኑ መጠን ከኢትዮጵያ ውጭ በመስራቱ ነው፡፡ ኩባንያው በተገቢው አክብሮት እንደሚያገለግለኝ እና ፍላጎቴን እንደሚያሟላልኝም ተስፋ አደርጋለሁ› ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል፡፡

ኩባንያው ‹የተሻለ አገልግሎት እና ማበረታቻ› በተለይም በጥራት እና ዋጋ ላይ ይዞ እንደሚመጣ ተስፋ በማድረግ የሳፋሪኮም ሲም ካርድ መግዛቱን አዲስ ይናገራል፡፡

ሌላኛው የሳፋሪኮም ደንበኛ የሆኑት ዮሴፍ ወርቀልዑል ከሳፋሪኮም በተሻለ ዋጋ ጥራት ያለዉ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደሚያገኝ ተስፋ እንደነበረዉ ይናገራል። ሆኖም ግን ዋጋዉ ውድ ሆኖ ማግኘቱን ለአዲሰ ስታንዳርድ ገልፀዋል፡፡

‹ያቀረበው የጥቅል አገልግሎትን ጨምሮ ዋጋው ምክንያታዊ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ከሳፋሪኮም የሚገኘው ወርሀዊ 100GB የኢንተርኔት ጥቅል 1000 የኢትዮጵያ ብር (2,290 የኬንያ ሺሊንግ) ከኢተዮ-ቴሌኮም ወርሃዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት ጥቅል ጋር እኩል ነው› ሲሉ ዮሴፍ ተናግሯል፡፡

‹ርካሽ እና ተመጣጣኝ አገልግሎት እንደማገኝ ተስፋ አድርጌ ነበር፤ ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ አሁን ባገኘሁት አገልግሎት ደስተኛ አይደለሁም› ስልም ዮሴፍ አክሏል፡፡

አዲስ በበኩሉ “ሳፋሪኮም ከኢትዮ-ቴሌኮም የተሸለ ነገር መስራት ካልቻለ ውድድሩን ተቋቁሞ መቀጠሉ ቀላል አይሆንለትም ብየ አስባለሁ” ብሏል፡፡

ሁለቱም ደንበኞች ኩባንያው በውል ወደ ገበያዉ ሲዘልቅ በተሸለ ጥራት እና በአንፃራዊ ርካሽ ዋጋ አዳዲስ አገልግሎቶችን እንደሚያስተዋውቅ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

ኩባንያው የሚታወቅበትን ኤምፔሳ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በኢትዮጵያ እንደሚጀምር ይፋ አድርጓል። ይህም እንደ ሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚው ፒተር ንዴግዋ ከሆነ “ለተጠቃሚዎች ዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ የበለጠ ትኩረት በማድረግ የንግድ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያሳድግ” ይጠበቃል፡፡

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ግሎባል ፓርትነርሺፕ ለኢተዮጵያ ተብሎ በሳፋሪኮም ኃ.የተ.የግ.ማ የሚመራ ድርጅት ሲሆን ከቮዳፎን ግሩፕ፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ሰሚቶሞ ኮርፖሬሽን እና የእንግሊዝ አለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ይጠቃለላል፡፡

በግንቦት ወር 2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ የግል የቴሌኮሙኒኬሽን ፍቃድ ለመስጠት ከመረጠቻቸው ሁለት ፍቃዶች አንዱን 850 ሚሊዮን ዶላር በማቅረብ እና 8.5 ሚሊዮን ዶላር በ10 አመት ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ በቀረበው መሰረት አሸናፊ መሆኑ ተገልፆ ነበር፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.