ዜና፡- የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ አስራ አንድ ክልሎች የማጅራት ገትር በሽታ በመከሰቱ 13 ሰዎች መሞታቸውን አስታወቀ

በጋምቤላ ክልል የማጅራት ገትር ክትባት ሲወስዱ
ምስል: የዓለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ ፣መጋቢት 30፣ 2014  – በአለም ጤና ድርጅት (WHO) በመጋቢት 25፣ 2014 ዓ.ም “ወረርሽኝ እና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች”  በሚል እትም ላይ የወጣ አዲስ ሪፖርት 13 ሰዎች መሞታቸውን (የጉዳት ገዳይ ጥምርታ (CFR) 0.9%) እና ለጥናቱ ከተመረጡ 12 ቦታዎች በ11ንዱ በሽታው እንደተገኘ እና  በአጠቃላይ 1,398 የተጠረጠሩ የማጅራት ገትር ተጠቂዎች መኖራቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል። ከነዚህም አራት ክልሎች፡- ኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ደቡብ፣ አማራ፣ “የወረርሽኙን ደረጃ አልፈዋል”፣ ሌሎች  አምስት ክልሎች:- ሀረሪ፣ አፋር፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ የማጅራት ገትር በሽታን “የማስጠንቀቂያ ጣራ አልፈዋል” ሲል ሪፖርቱ ገልጿል። 

በኦሮሚያ ክልል 610 ሰዎች (44%) በቫይረሱ ​​የተያዙ ሲሆን፥ በሶማሌ ክልል 211 (15%) የቫይረሱ ​​ተጠቂዎች ይገኛሉ። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በኢትዮጵያ የማጅራት ገትር በሽታ እ.ኤ.አ 2021 ከ49 ኛው ሳምንት ጀምሮ  እስከ ታኅሣሥ 12 ማብቂያ ድረስ ሲንሰራፋ እንደነበር ተጠቅሷል።

“በአጠቃላይ የማጅራት ገትር በሽታ ተጠቂዎች ናቸው ተብለው ከተጠረጠሩት አምስት ክልሎች ማለትም ኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ደቡብ፣ አማራ እና ሀረሪ 87.8% (1228 ሰዎች) አስመዝግበዋል።  የኦሮሚያ ክልል በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳ ሲሆን 610 ሰዎች (44%) ፣ በመቀጠል የሶማሌ ክልል 211 ሰዎች (15%)፣ ደቡብ ክልል 154 ሰዎች (11%) ተጋልጠዋል።”

ሪፖርቱ ኢትዮጵያ “በትጥቅ ግጭቶችም ሆነ በተፈጥሮ አደጋዎች ከተጠቁት” የአፍሪካ ሀገራት አንዷ መሆኗን ጠቅሶ ድርቅ፣ የበሽታ ወረርሽኝ እና  እየተንሰራፋ ያለውን የማጅራት ገትር በሽታ ጨምሮ በሪፖርቱ አካቷል። “የማጅራት ገትር በሽታ ወረርሽኝ በአንጻራዊ ሁኔታ ዝቅተኛ CFR ቢያሳይም በሽታው ወደባሰ ቀውስ እንዳይሄድ ለመቆጣጠር የሚያስችሉ   አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎች መተግበር እና   መከላከል አስፈላጊ ነው።” ሲል ሪፖርቱ ያትታል። 

ለፈጣን ምላሽ ቡድኖች የቅድመ-ሥምሪት ስልጠና ተሰጥቷል። እንዲሁም የላቦራቶሪ አስተዳደር አቅምን ማሳደግ እንደቀጠለ ሲሆን  በማጅራት ገትር በሽታ ከተጠረጠሩ ሰዎች  ሴሬብሮስፒናል ፈሳሾች (cerebrospinal fluid) መሰብሰብ ቀጥሏል። “ናሙናዎች ወደ ክልላዊ ሪፈራል ላቦራቶሪዎች እየተላኩ ነው። መንግስት ጉዳዩን በበቂ ሁኔታ የሚቆጣጠር አካል መኖሩን በማስተማመን ላይ ይገኛል። ጉዳዩን  ለመቆጣጠር የሴፍትሪአክሰን አንቲባዮቲክ (Ceftriaxone antibiotic) ጥያቄ ለአለም አቀፍ አስተባባሪ ቡድን (ICG) ቀርቧል” ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ተናግሯል።

ነገር ግን የባክቴሪያ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ምርመራ መዘግየትን ለመከላከል እና አስፈላጊውን ክትባት በወቅቱ ለመጠየቅ  የሀገር ውስጥ የላቦራቶሪ አቅም ግንባታ ቀዳሚ ተግባር ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባ  በሪፖርቱ ምክረ ሃሳቡን አስፍሯል።”የብሔራዊ ባለስልጣናት እና አጋሮች ለጉዳይ አያያዝ በቂ ገንዘብ፣ሎጂስቲክስ እና መድሃኒት መስጠት አለባቸው” ተብሏል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.