ትንተና: ከጦርነት ሽሽት እስከ አዲስ አበባ ጎዳናዎች የልመና ኑሮ – የዋግ ኽምራ ዞን የተፈናቃዮች አስከፊ ህይወት

በእቴነሽ አበራ

አዲስ አበባ ፣መጋቢት 30፣ 2014 – በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፊጋ ሳህሊተ ምህረት የትራፊክ መብራት ዙሪያ ጥቂት የማይባሉ ጨቅላ ህፃናትን በጀርባቸው ያዘሉ ወጣት ልጃገረዶች መኪና እየዞሩ ገንዘብ ሲለምኑ ይታያሉ። ይህ ትዕይንት በአዲስ አበባ ከተማ ያልተለመደ ነገር አይደለም። ነገር ግን እነዚህ ልጃገረዶች እንደሌሎች በመዲናዋ በልመና የሚተዳደሩ የጎዳና ተዳዳሪዎች ሳይሆኑ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን ጦርነቱን ሸሽተው፣ የሚተዳደሩበትን የግብርና ስራ ጥለው የተሰደዱ ተፈናቃዮች ናቸው።

ስላሥ እድሜዋ 18 ሲሆን፣ የአንድ ልጅ እናት ናት። “አዲስ አበባ በእግር ለመድረስ ሁለት ሳምንት ፈጅቶብናል” ስትል የምትናገረው  ስላሥ የቤተሰቦቿ ኑሮ በእርሻ ላይ የተመሰረተ ነበር። አሁን ግን የሚረዳቸው ስለሌለ በልመና ላይ ተሰማርተው ኑሯቸውን ለመምራት ተገደዋል። በፌዴራል መንግስት እና በትግራይ ተዋጊ  ኃይሎች መካከል ባለው ጦርነት የተነሳ  ከባለቤቷ ጋር በመሆን ነው ወደ አዲስ አበባ የመጣችው። መቱ ሌላኛዋ የተፈናቀለች እናት ስትሆን እድሜዋ 20 ነው። ነፍሰ ጡር  ሆና ከዋግ ኽምራ ወደ አዲስ አበባ (750 ኪ.ሜ. አካባቢ) ድረስ ተጉዛ የደረሰች ሲሆን ” አዲስ አበባ ከመጣሁ በኋላ ነው ልጄን የወለድኩት ስትል ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግራለች ።  መቱ አሁን ላይ የ3 ወር ሕፃኗን በጀርባዋ ይዛ ትዞራለች።

እንደ ስላሥ እና መቱ ወደ አዲስ አበባ  መመጣት ያልቻሉት ተፈናቃዮች በሰቆጣ፣ ወለህ እና ዝቋላ ወረዳዎች ተጠልለው ይገኛሉ። መጋቢት 22 የዋግ ኽምራ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ባወጣው መረጃ መሰረት የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከ65,000 መብለጡን አስታውቋል። በአጠቃላይ 16,376 ሰዎች  የተፈናቃዮች ማዕከላት ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን 49,381 ሰዎች ከማህበረሰቡ ተጠግተው የሚኖሩ እንደሚገኙ የሚያትተው መግለጫው “ከአጠቃላይ ተፈናቃዮቹ 20,000 ያህሉ ከጻግብጂ  ወረዳ የመጡ መሆናቸውን” ገልጿል።

የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ፌስቡክ ገፅ የዞኑን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደስታ ጌታሁንን ወቢ አድርጎ በቀን ከ2000 ሰዎች በላይ ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ በመሆኑ ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱን ገልጿል።

በመጋቢት ወር የሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኢሳያስ ሞገስ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በዋግ ኽምራ ዞን ስር ከሚገኙት ስምንት ወረዳዎች መካከል የተወሰኑት አሁንም በትግራይ ታጣቂ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መኖናቸውን ገልፀው  አበርጋሌ እና ጻግብጂ ሙሉ በሙሉ  በቁጥጥራቸው ስር ናቸው ብለዋል። ኃላፊው አክለውም በሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ሶስት ቀበሌዎች እና የዙቋላ ወረዳ አራት ቀበሌዎችም ጭምር በትግራይ  ታጣቂ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ሲሆኑ ለጊዜው ምንም አይነት ጦርነት ባይኖርም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ክልል ሀይሎች እነዚያን ቦታዎች አለቀቁም ብለዋል።

የተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር

በአማራ ክልል ከ11 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ህዝብ የእለት ምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበርያ ኮሚሽን አስታውቋል። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኢያሱ መስፍን ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ፤ ለሰዎች መፈናቀልና ሰብዓዊ ርዳታ የሚያስፈልግበት የተለያዩ ምክንያቶች ውስጥ፣ ግጭት ቀዳሚ መንስኤ ነው በማለት ገለፀዋል።

በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በተፈጠረው ግጭት ከ900,000 በላይ መሰሰዳቸውን፣ 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ከትግራይ ኃይሎች ጋር በተፈጠረው ግጭት መፈናቀላቸውን፣ የተቀሩት 9.3 ሚሊዮን ተፈናቃዮች ደግሞ በክልሉ በጦርነት ከተጎዱ አካባቢዎች መሆናቸውን አቶ እያሱ ገልጸዋል። ከኦሮሚያና ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ ተፈናቃዮች በምዕራብ ጎጃም ፣ሰሜን ሸዋ ፣ደቡብ ወሎ እና ዋግ ኽመራ ዞኖች ተጠልለው እንደሚገኙ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አክለው ገልጸዋል። በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና  ኮሚሽን እንደገለጸው ተፈናቃዮቹ በወር ቢያንስ 1.2 ሚሊዮን ኩንታል እህል ያስፈልጋቸዋል።

አቶ እያሱ አያይዘውም በትራንስፖርት እጥረት የተነሳ ኮሚሽኑ ሰፋፊ ቦታዎችን እንዳይሸፍን እያደረገው ቢሆንም ከፌዴራልና ከክልል መንግስታት፣ ከክልል መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ከህብረተሰቡ እርዳታ እየደረሰ እነደሆነ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ባወጣው ሪፖርት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዋነኝነት ከትግራይ እና አዋሳኝ አካባቢዎች እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል በግጭት እና ሁከት መፈናቀላቸውን አመልክቷል። አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ከትግራይ ክልል ደቡብ ዞን ራያ አላማጣ፣ ኦፍላ፣ ዛታ፣ ኮረም እና ራያ አዘቦ ወረዳዎች ተፈናቅለዋል ሲል ዘገባው አመልክቷል።

የጤና አገልግሎቶች እጥረት

የሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳያስ እንደገለፁት ችግሩ ከዞኑ አስተዳደር አቅም በላይ መሆኑን በመግለጽ የክልሉ መንግስት ከፍተኛውን ድርሻ እያበረከተ መሆኑንና በተፈናቃዮች መጠለያዎች ላይ ችግር የሚፈጥረው የጤና አገልግሎት እጦት መሆኑን አስምረውበታል።

የሰቆጣ ጤና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታምሩ ይምራው በበኩላቸው “የተላላፊ በሽታ መከሰት ስጋት አሳሳቢ ነው” ያሉት ሀላፊው “49,000 ህዝብ ያላት ከተማ ከ170,000 በላይ ተፈናቃዮችን እያስተናገደች ነው” ያሉ ሲሆን  በመቀጠልም “በነበሩን የህክምና መሳሪያዎች ሁለት ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮች ከፍተናል። በየቀኑ ከ60-150 ታካሚዎችን እናስተናግዳለን ብለዋል። አቶ ታምሩ በተፈናቃይ መጠለያዎች ውስጥ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን አስፈላጊነትንም አብራርተዋል። እንደ አቶ ታምሩ ገለጻ የጤና ቢሮው ተላላፊ በሽታዎችን የመከላከል ስራ እየሰራ መሆኑን የገለፁት መሰል በሽታዎች መደበኛ ባልሆኑ መጠለያዎች ውስጥ በመስፋፋታቸው ነው። የመጸዳጃ ስፍራዎች እጦት ለተላላፊ በሽታዎች  ተጋላጭነት እንዲጨምር ያደርጋል ብለዋል።

“ከአበርገሌ ወረዳ በመጡ ተፈናቃዮች ላይ የእከክ በሽታ ታይቷል” ያሉት ዳይሬክተሩ  “ከመስፋፋቱ በፊት እንዳይተላለፍ ልንቆጣጠረው ችለናል” ብለዋል። መጠለያዎቹ ውሃ፣ ምግብ እና መጸዳጃ ስፍራዎች እንደሌላቸውመ ሀላፊው አስረድተዋል። ትልቁ ችግር ትክክለኛ መጸዳጃ ስፍራዎች አለመኖሩ ነው ያሉት አቶ ታምሩ ወረርሽኙ ቢከሰት ቀውስ ሊፈጠር እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል። የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራም ጠይቀዋል።

የመድሃኒት እጥረት

ችግሩ በዚህ ብቻ አያቆምም። የአበርገሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አለሙ ክፍሌ በቅርቡ ለቪኦኤ አማርኛ በሰጡት ቃለ ምልልስ በምግብና በመድኃኒት እጥረት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 120 መድረሱን ገልጸዋል።እንደ እርሳቸው ገለጻ፣

የህጻናትና አረጋውያን ሞት ከፍተኛውን የሟቾች ቁጥር የሚይዝ ሲሆን እንደ ጎልማሶች በኤች አይ ቪ እና የደም ግፊት ያሉ የጤና እክል አና በመድኃኒት እጦት እንዱሁም ሕፃናት  በወባ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

የምግብ እጥረት, ለህጻናት  የተመጣጠነ ምግብ እጥረት

የዞኑ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ከፍያለው ደባሽ ለቢቢሲ አማርኛ እንደተናገሩት በምግብ እጥረት የተጎዱ ህጻናት አፋጣኝ እርዳታ እስካልተደረገ ድረስ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸዋል ። “አሁን ሕፃናት አፋቸውና አፍነጫቸው ቆስሏል። እንደተላላፊ በሽታ ይህ እያደገ ይሄድና ከ77ቱም የበለጠ እልቂት ሊኖር ይቸላል። ምግብ የሌላቸው ሕፃናት በሽታ ሲጨመርባቸው የሚከሰተው ችግር ቁልጭ ብሎ የሚታይ ነው” ሲሉ ተናግረዋል ። 

ሀላፊው የተለያዩ አካባቢዎች በትግራይ ሀይሎች መያዛቸውን እና በቆላማ አካባቢዎች የሚገኙ አብዛኞቹ ወረዳዎችን ካጠቃው ድርቅ ጋር ተደምሮ ከ61 ሺህ 600 በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን ተናግረዋል። ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት 151,000 ሰዎች በምግብ ዋስትና ፕሮግራም ላይ ጥገኛ መሆናቸውንም  አስታውሰዋል።

አስፈላጊው የማህበራዊ አገልግሎት በሚፈለገው መጠን አለመኖሩ የወረዳው ትልቁ ችግር እንደሆነ ኃላፊው ተናግረዋል። አቶ ከፍያለው፣ አበርገሌ፣ ጻግብጂ እና ዝቋላ ወረዳ እና ሌሎች 6 ቀበሌዎች አሁንም በትግራይ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ያሉ መሆኑን ገልፀው በተጨማሪም ከእነዚህ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን መመለስ ለተፈናቃዮቹ ቀውስ ”ዘላቂ መፍትሄ” እንደሚሆን አአስረድተዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.